የክረምት የ90 ቀናት እና የ2019 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ ተካሄደ
ITDB፦ መስከረም 27/2018 ዓ.ም
በአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት በሮ የክረምት የ90 ቀናት እና የ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ አመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ ተካሄደ።
በመርሃ ግብሩ የቢሮ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ ብድን መሪዎችና ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን የመርሃ-ዓላማ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የክረምት 90 ቀናት የሰው ተኮር ሥራዎች በልዩ ትኩረትና በፈጣን ምላሽ ተግባራዊ በመደረጉ የተከናወኑት ተግባራት ላይ ትኩረት ያደረገ ዉይይት ማካሄድ ነው።
የቢሮው ኃላፊ አቶ አዋሌ መሐመድ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዉ የዕቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ መኮንን ሞጣሎ ሪፖርቱን ያቀረቡ ሲሆን በቀረበው ሪፖርት ላይ መሰረት ያደረገ ውይይት ተደርጓል። በዉይይቱም ተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶችን ያነሱ ሲሆን ጽ/ቤት ሀላፊዉ እና ም/ቢሮ ሀላፊዎች ምላሽ ሰጥተዉበታል።
በመጨረሻም የቢሮ ሀላፊ በአቶ አዋሌ መሀመድ ማጠቃለያ በመስጠት የዉይይት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
See less
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments