
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የቴክኖሎጂ መመርያ ላይ መሰረት ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
ITDB ግንቦት 13/2017 ዓ.ም
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የቴክኖሎጂ መመርያ ላይ መሰረት ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለቢሮ ሰራተኞች ተሰጠ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነዋሪዎች እና ለጎብኚዎች ምቹ እንድትሆን ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወነ ይገኛ። በዚሁ መሰረት ሁሉም የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት፣ ክ/ከተማዎች እና ወረዳዎች እንደየመስርያ ቤታቸው ሁኔታ ደህንነታቸው የተጠበቀና የተቀናጁ ቴክኖሎጂዎች በአግባቡ ተጠቅመዉ አገልግሎት አሰጣጣቸውን ለማዘመንና የተገልጋዩችን እርካታ እንዲሻሻል በማስፈለጉ በከተማ አስተዳደሩ ስር ያሉ ተቋማት የቴክኖሎጂ አጠቃቀማቸዉ እያደገ መጥቷል።
ይሁን እንጂ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ተቋማት ቴክኖሎጂን የማልማትና የማስተዳደር ስልጣን ከተሰጠው ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እዉቅና ዉጪ በራሳቸው ሲስተም እያለሙ ሲሆን የማይናበቡና ደህንነታቸው ያልተረጋገጠ ሲስተሞች ለቁጥጥር አመቺ ባለመሆኑና ለሳይበር ጥቃት ተጋላጭ፣ ለብልሹ አሰራር እንዲሁም የመንግስት መረጃን ጭምር ለአደጋ የሚዳርግ ስለሆነ የቴክኖሎጂ የአሰራርና የቁጥጥር ስርዓት መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር እንደገና በመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 84/2016 አንቀፅ 15 ንዑስ አንቀፅ 2 መሰረት ይህንን መመሪያ በማዉጣቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የቴክኖሎጂ መመርያ ላይ መሰረት ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በአቶ ወርቁ መሳፍንት አማካኝነት ተሰጥቷል።
በስልጠናውም የፈፃሚ አካላት ተግባር እና ሀላፊነት በዝርዝር ተዳሰዋል። ከዚህም ባሻገር መመርያዉ ላይ መሰረት ያደረገ ሀሳብ እና አስተያየት ከተሳታፊዎች የተነሱ ሲሆን በአሳልጣኙ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments