የ2019 በጀት ዓመት ከጥቅምት 1 እስከ 15 የ...

image description
- In Training    0

የ2019 በጀት ዓመት ከጥቅምት 1 እስከ 15 የተከናወነ እቅድ አፈፃፀም ስራዎች ተገመገመ

ITDB፦ጥቅምት 18/2019 ዓ.ም

በመርሃ-ግብሩ የቢሮው አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች የተገኙ ሲሆን መርሃ ግብሩን የመሩት የቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተው የዉይይቱ ዓላማ የ90 ቀን እቅድ ላይ ተወያይቶ የጋራ ማድረግ ላይ የሚያተኩር መሆኑን ገልጸዉ ዕቅዱን ሁሉም መረዳት እንደሚገባውና የጋራ ግንዛቤ ሊኖረው እንደሚገባም በማመላከት የሚላኩ ሪፖርቶች በጥንቃቄ መሰራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኛቸዉ ፈለቀ ይህን መሰል ተግባር አገልግሎታችንን ለማሳለጥ የሚረዳን በመሆኑ በየ15 ቀኑ ሪፖርቱን አዘጋጅቶ በሳምንቱ መጨረሻ ገቢ ማድረግ እንደሚገባ አመላክተዋል። በተያያዘም የቢሮ የእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ መኮንን ሞጣሎ የ2ኛ ሩብ አመትን የመጀመሪያ 15 ቀናት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ከዚሁ ጋር የቢሮው የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግርማ ከበደ በመልካም አስተዳደር፣ ቅሬታና አቤቱታ አፈታት ውሳኔ አሰጣጥና አፈፃፀም ላይ የ90 ቀናት ሪፖርት አቅርበዋል።

የክትትልና ድጋፍና የሱፐርቪዢን ቡድኖች ቢሮዉን በመጎብኘት ያዩትን ጥንካሬና ክፍተት የቀረበ ሲሆን በአመራሮችና በሚመለከታቸው ክፍሎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

በመጨረሻም የታዩትን ክፍተቶች ከተሰጠው ግብረ መልስ አኳያ ፈጥኖ ማስተካከል እንደሚገባ በመግለፅ ውይይት ተጠናቋል።

#AddisSmartcity

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714

See less


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments