ጳጉሜ 4 የህብር ቀንን በማስመልከት “ማዕድ ማጋ...

image description
- In Training    0

ጳጉሜ 4 የህብር ቀንን በማስመልከት “ማዕድ ማጋራት” የማጋራት መርሃ ግብር ተካሄደ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጳጉሜ 4 የሚከበረውን የህብር ቀንን ምክንያት በማድረግ ለአዲስ ከተማ ክ/ከተማ መቶ አቅመ ደካሞች በመተሳሰብና በመረዳዳት መንፈስ ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር ተካሄደ።

በመርሃ ግብሩ የቢሮ ዓመራሮች የተገኙ ሲሆን የመርሃ ግብሩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ስማርት ሲቲ ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር አብሮነትና መተሳሰቡ የሚያጎለብት መሆኑን ገልፀዉ የህብር ቀንንም በተግባር ያየንበት ቀን ነው እንዲሁም በዚህ የመረዳዳት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው አቅመ ደካሞች በዚህ የበዓል ወቅት ተቋሙ አቅመ ደካሞችን ከግምት ያስገባ ድጋፍ በማድረጉ የተሰማቸዉን ደስታ ገልፀዋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714

See less


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments