የ2019 በጀት ዓመት ስትራቴጂክ ግቦች፣ ዓላማዎ...

image description
- In Training    0

የ2019 በጀት ዓመት ስትራቴጂክ ግቦች፣ ዓላማዎች እና ዝርዝር ተግባራት ዙርያ የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ለ2019 በጀት ዓመት ለሴክተር ተቋማት ICT ዳይሬክተር እና ለክ/ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን የሚወርድ ስትራቴጂክ ግቦች፣ ዓላማዎች እና ዝርዝር ተግባራት ዙርያ የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ።

በመድረኩ የቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ፣ የቢሮ ዳይሬክተሮች፣ የተቋማት ICT ዳይሬክተሮችና የክ/ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን መሪዎች ተገኝተዉበታል።

የመድረኩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተዉ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላፈዉ የዛሬዉ መርሃ ግብር ዓላማ ከእስዛሬዉ በተለየ ከቢሮ ዘርፎች ጋር ዕቅድና መከናወን ስለሚገባቸው ተግባራት በመወያየት በዕቅድና በጀት ዳሬክቶሬት አማካኝነት ተጠምሮ ዛሬ ለዉይይት እንደሚቀርብ ገልፀዉ ይህንን መሰረት በማድረግ ወጥ የሆነ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት የሚያስችል ሁኔታ መኖሩን በማመላከት መልካም የዉይይት ግዜን ተመኝተዋል።

የዕቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ መኮንን ሞጣሎ ለ2019 በጀት ዓመት ለሴክተር ተቋማት ICT ዳይሬክተር እና ለክ/ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን የሚወርድ ስትራቴጂክ ግቦች፣ ዓላማዎች እና ዝርዝር ተግባራትን ያቀረቡ ሲሆን ይህንን መሰረት በማድረግ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄዎች ተነስተዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የተሰጡ አስተያየቶችን እንደግብዓት በመዉሰድ የቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተዉ ለጥያቄዎቹ ምላሽ ሰጥተዋል። በመጨረሻም በቀጣይ መከናወን ስለሚገባቸው በ2019 አገልግሎቶችን ኦንላየን እንደሚደረግና ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት እንደሚገባ፣ ዲጅታል 2030 ዕዉን ለማድረግ ቢሮዉ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለዉና ከዚህ ጋር በተያያዘ ክ/ከተማና ሴክተር ተቋማት ከፍተኛ ሀላፊነት እንዳለበት፣ ዕቅድ ስናቅድ ከተቋማችን ባለፈ የከተማዉን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ መሆን እንደሚገባዉ አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።

#AddisSmartcity

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714

See less


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments