የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ

image description
- In Training    0

የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ

ITDB፦ ሰኔ 2/2017ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሳምንታዊው የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ። በዚህ መርሃ ግብር ዕውቀት ሽግግር መርሃ-ግብር ላይ የቢሮው አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች እና ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን “የዛሬው ቀን ፋይዳ” በሚል ርዕስ የቢሮው ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ግሩም አብተው የዕውቀት ሽግግር አድርገዋል። በየቀኑ የምንሰራቸውን ነገሮች ካልቀየርን ህይወታችንን መቀየር እንደማንችል እና ለነገው ብቁ ዝግጅት የምናድርገው ዛሬን በአግባቡ ስንጠቀም መሆኑን ገልፀዋል። በመጨረሻም ትኩረት በሚፈልጉ ስራዎች ላይ አቅጣጫን በማመላከት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments