በጤናዉ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከት የሚች...

image description
- In Training    0

በጤናዉ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችል AI Assisted teleradiology በየካቲት12 ሆስፒታል በዛሬዉ ዕለት ወደ ስራ አስገብቷል

ITDB ግንቦት 28/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከተማዋን እንዲሁም አገልግሎት አሰጣጥን ከማዘመን አንፃር የስምንት ዓመት የስማርት ሲቲ ስትራቴጂክ ፕላን አፅድቆ ወደ ስራ ካስገባ ሶስት ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ከስማርት ሲቲ ስድስት ምሶሶዎች አንዱ የሆነዉን ስማርት ሊቪንግ ላይ መሰረት ያደረገ በጤናዉ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችል AI Assisted tele radiology መቀመጫውን ሰሜን ኮርያ ያደረገዉ ራዲሰን ካንፓኒና ጤና ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በየካቲት12 ሆስፒታል በዛሬዉ ዕለት ወደ ስራ አስገብቷል።

የመርሃ ግብሩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የስማርት ሲቲ ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በመጠቀም በሀገራችን ያለዉን ዉስን የራዲዮሎጂስቶችን እጥረት የሚቀርፍ ከተለያዩ ክልል ከተሞች በሪፈር ወደ አዲስ አበባ የሚመጡትን ህሙማን ያለምንም እንግልት ጥራቱን የጠበቀ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እና በርካታ የጤና እክሎችን መለየት የሚያስችል AI Assisted teleradiology ወደ ስራ የማስገባት ዕለት መሆኑን አብስረዉ በተያያዘም በቀጣይ እነዚህን መሰል ማሽኖች ተደራሽነት በማስፍት ህሙማን በወቅቱ ህክምና እንዲያገኙ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚበረክት በማመላከት በቀጣይ ከተለያዩ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን መሰል ማሽኖችን በመጠቀም የአኗኗር ዘያችንን የማሻሻል ተግባር እንደሚከናወን ጠቁመዋል።

የራዲሰን ካንፓኒ AI ኢንጅነር የአፍረካ ቢዝነስ ዲቨሎፕመንት ሊድ ዶ/ር ደሳለኝ በበኩላቸው ይህ AI Assisted teleradiology ማሽን በጤናዉ ዘርፍ ከፍተኛ አገልግሎት ያለዉና መረጃዎችን በአግባቡ አደራጅቶ በማስቀመጥ የሲንየር ራዲዮሎጂስቶችን የስራ ጫና የሚቀንስ እንዲሁም ጀማሪ ራዲዮሎጂስቶችን የሚያግዝ መሆን ገልፀዉ በቀጣይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በቴሌራዲዮሎጂ ፕላትፎርም በክላዉድ አማካኝነት ካሉበት ስፍራ የኤክስሬ ዉጤት በማየት ሪፖርት የሚላክበት መንገድ እንደሚመቻች አመላክተዋል።

የየካቲት12 ሜዲካል ኮሌጅ ስራ አስኪያጅ ዶ/ር አንተነህ ምትኩ ይህ የጂጅታል ጤና አካል የሆነዉ AI Assisted teleradiology ማሽን ታካሚዎች ያሉበት የህክምና ክፍል ዉስጥ ሆነው የሚገለገሉበትና መረጃዎችን በማደራጀት ከህክምና ባሻገር ለጥናትና ምርምረ መጠቀም የሚያስችል መሆኑን አመላክተዋል። በመጨረሻም የየካቲት12 ሜዲካል ኮሌጅ ኤክስፐርት ሜዲካል ራዲዮሎጂስት ሳሙኤል አስፍዉ ማሽኑ አጠቃቀም በተመለከተ አጭርና ግልፅ ማብራሪያ ተሰጥተዋል

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments