የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖ...

image description
- In Training    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሰራተኞች "ብቃት ያለዉ ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብልፅግና" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ መነሻ በማድረግ ዉይይት አካሄዱ።

ITDB፦ ግንቦት 27/2017 ዓ.ም

የዉይይት ዋና ዓላማ የሀገራዊ ለዉጡ የእስካሁን ጉዞና የደረሰበት ደረጃ ከሲቪል ሰርቪሱ ተልእኮ አንፃር በሚገባ መረዳት እና የሀገራችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ለምናደርገው ጥረት የሲቪል ሰርቪሱ ሚና እጅግ ወሳኝ መሆኑ መግባባት ላይ መድረስ እና ሀገራችን የነደፈችው የብልፅግና ጉዞ ለማረጋገጥ የሲቪል ሰርቪሱ ሚና ማሳየት ነው።

ሰነዱ በተንቀሳቃሽ ምስል በመታገዝ ያቀረቡት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስ ሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ ክብር ዶ/ር ጀማሉ ጀንበሩ ሲሆኑ በሰነዱ በዋናነት ከተነሱ ፅንሰ ሀሳቦች መካከል፦ ሀገሪዊ ለዉጡ ያስመዘገባቸው ዉጤቶችና የሲቪል ሰርቫንቱ ሚና፣ የሲቪል ሰርቪሱ አሁናዊ ሁኔታ፣ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል የሲቪል ሰርቪሱ ሪፎርም እና መፍትሔ፣ ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች በዝርዝር አብራርተዋል።

በተያያዘም ሰነዱ ላይ መሰረት ያደረገ ዉይይት በቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ፣ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ነብዩ ፍቃዱና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተዉ መሪነት የተካሄደ ሲሆን ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች ተነስተዋል። የተነሱ ሀሳብ አስተያየቶችን እንደግብአት በመዉሰድና በጋራ መግባባት የቢሮ አመራሮች ምላሽ ሰጥተዉበታል። በመጨረሻም ተቋሙን ወክለዉ በከተማ ጀረጃ ዉይይት የሚያካሂዱ ዘጠኝ የቢሮ ሰራተኞች ምርጫ በማካሄድ መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments