የወርቃማ ሰኞ ማለዳ የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብ...

image description
- In Training    0

የወርቃማ ሰኞ ማለዳ የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ

ITDB፦ ግንቦት25/2017ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ ::

በመድረኩ ላይ የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ፣ ም/ቢሮ ሀላፊዎች፣ ጽ/ቤት ሀላፊና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

በዕለቱ Human temperaments በሚል ፅንሰ ሀሳብ ላይ መሰረት ያደረገ የልምድ ሽግግር ያካፈሉት የቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተዉ choleric, sanguine, phlegmatic, melancholic የመሳሰሉ የመረዳት አቅማችንና በዕለት ተዕለት ኑሮአችን ሊረዱን የሚችሉ ባህርያት ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥተዋል።

በመጨረሻም ሳምንታዊ የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እና የቀጣይ ሳምንት የትኩረት አቅጣጫዎች እንዲሁም ዕቅድና ሪፖርት በምን መልኩ መቅረብ እንዳለበት አቶ ግሩም አብተዉ ጠቅሰው ሁሉም ባለሙያዎችና አመራሮች ስራን ያማከለ የተደራጀ መረጃ በማቅረብ ለውጤታማነት በጋራ እንትጋ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments