የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር

image description
- In Technology Trends    0

የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር

ITDB፦ ግንቦተ 18/2017ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሳምንታዊው የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተከናወነ። በዚህ መርሃ ግብር ላይ የቢሮው አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች እና ሰራተኞች የተገኙ ሲሆኑ “7ቱ የስኬታማ ሰዎች ልማዶች በሚል ርዕስ የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አዋሌ መሃመድ የዕውቀት ሽግግር አድርገዋል። በዕውቀት ሽግግሩም ውስጥ ሰባቱን የስኬታማ ሰዎች ልማዶች ማለትም ንቁ መሆን፣ በአእምሮ በመጨረስ መጀመር፣ መቅደም ያለበትን ማስቀደም፣ የጋራ ስኬትን ማሰብ፣ ተረድቶ ማስረዳትን፣ በአብሮነት መረዳዳት፣ መደጋገፍ እና ግለቱን ሳይለቅ ማስቀጠል በሚሉ ንዑስ ርዕሶች ላይ ሰፊ ማብራሪያ የተሠጠ ሲሆን የሳምንቱን ቀጣይ የስራ አቅጣጫ በመስጠት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments