የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖ...

image description
- In Technology Trends    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈፃፀም በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተገመገመ

 

ITDB፦ ግንቦት 14/ 2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከሚደግፋቸዉ ዘጠኝ ተቋማት መካከል አንዱ ነው። በመሆኑም የግምገማ ዓላማ የቢሮው የ2017 የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈፃፀም ምን እንደሚመስል፣ በዘጠኝ ወራት የታቀደው ዕቅድ መከናወኑን መገምገምና ክፍተቶች ካሉ ድጋፍ ማድረግ ላይ ያለመ ነው።

የቢሮ ዕቅድና በጀት ዳሬክተር አቶ ሀብቱ አርብሴ የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን የቀረበዉ ሪፖርት ላይ መሰረት በማድረግ ከቋሚ ኮሚቴው አባላት የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች ተነስተዋል። ከነዚህም መካከል በበጀት አመቱ የነበረዉ አፈፃፀም ጥሩ እንደነበርና ከሳይበር ደህንነት ጋር በተያያዘ በቢሮ አማካኝነት ለተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መከናወኑ የሚበረታታ ተግባር መሆኑን ገልፀዉ አሁን ካለዉ ጥሩ እንቅስቃሴ ባሻገር ተቋማትን ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ ከማዘመንና ማቀናጀት አንፃር የተሻለ ስራ መሰራት እንዳለበት፣ በአመራር ደረጃ የሴቶች ተሳትፎ ከፍ ማድረግ እንደሚገባ፣ ቢሮዉ የቴክኖሎጂ ተቋም ከመሆኑ አንፃር የፈጠራ ስራዎችን የሚሰሩ ታዳጊ ልጆች ለማበረታታትና የተቋማትን ዌብሳይት ማልማት አንዲሁም መቆጣጠር ላይ ምን ተከናወነ የሚሉ ርዕሰ ጉያዮች በዋናነት አንስተዋል።

በተያያዘም በተነሱ ሀሳብ አስተያየቶች ላይ ም/ቢሮ ሀላፊዎችና ፅ/ቤት ሀላፊ ምላሽ የሰጡበት ሲሆን የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ለአፍሪካ ተምሳሌት የሆነች ከተማ ለመፍጠር ቢሮዉ እየሰራ መሆኑንና የለሙ ሲስተሞችን ከመከታተል እና ከመቆጣር አንፃር አሁን ያለዉ የቁጥጥር ስርዓት በተሻለ ደረጃ ከፍ የሚያደርግ ስርዓት እየተዘረጋ መሆኑ ገልፀዉ የምክር ቤቱን ድጋፍ የሚሹ ጉዳዬች አስቀምጠዋል። ከተቀመጡ ጉዳዮች መካከል በዋናነት ባለሙያን ከማቆየት አንፃር የደመወዝ ጭማሪንና ግብዓትን በተመለከተ ድጋፍ እንደሚሹ አመላክተዋል።

በመጨረሻም የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ጋትዌች ተቋሙ በአለም አቀፍ ደረጃ በፍጥነት እያደገ የመጣውን በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት ከግምት ውስጥ በማስገባት ከዚህ የበለጠ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments