
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አጠቃላይ ካዉንስል ሳምንታዊ የስራ ግምገማና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ መሰረት ያደረገ ዉይይት አካሄደ
ITDB፦ ግንቦት 13/2017ዓ.ም
አጠቃላይ ካዉንስል ሳምንታዊ የስራ ግምገማና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ መሰረት ያደረገ ዉይይት በቢሮው ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ አማካኝነት የተካሄደ ሲሆን ዉይይቱ ትኩረት ካደረገባቸው ርዕሰ ጉዳዮች መካከል ሳምንታዊ ዕቅድና ሪፖርት አፈፃፀም፣ የ2018 በጀት ዓመት ካፒታል በጀትን በተመለከተ፣ የኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ስልጠናን ለመዉሰድ ለተቋሙ ሰራተኞች ምቹ ሁኔታን መፍጠር እና ሲስተም ስታንዳርዳይዝ ማድረግ ላይ ቤቱ በሙሉ ድምፅ የተስማማባቸው አጀንዳዎች ላይ ዉይይት ተካሂዷል።
በዉይይቱም በሳምንት ዉስጥ ምን ተሰራ፣ በቀጣይ መሰራት ያለባቸው ተግባራት ማቀድ፣ የአቅም ክፍተት የሚስተዋልባቸዉ እንዴት የማብቃት ስራ መሰራት እንዳለበት፣ ያጋጠሙ ችግሮች እንዲሁም የመፍትሄ ሀሳቦች በተመለከተ ተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳብ አስተያየታቸዉን በመስጠት የሳምንቱ መርሃ ግብር ተጠናቋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments