
በምስራቅ አፍሪካ የመጀመርያ የሆነው የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ (ETEX 2025)
በምስራቅ አፍሪካ የመጀመርያ የሆነው የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ (ETEX 2025)
*************
ITDB፦ግንቦት 8/2017 ዓ.ም
በኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ክቡር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተከፈተው እና በምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የሆነው የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ (ETEX 2025) የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች እና የዘርፉ ምሁራን በተገኙበት በዛሬው እለት በይፋ ተጀምሯል።
ሃገራችን ለዘርፉ በሰጠችው ትኩረት የቴሌኮም አገልግሎቶች እና የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ስራዎች፣ ዲጂታል መታወቂያ፣ የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ፣ የመንግሥት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል የማስገባት ስራዎች እንዲሁም ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አስተዋዋቂነት የስማርት ከተማ ልማት የመሳሰሉት በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ መሰረት የሚጥሉ ስራዎች ያመጧቸው ተጨባጭ ማሳያዎች በኤክስፖው እየተጎበኙ ይገኛሉ።
ኢትዮጵያ ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለሰጠችው ትኩረት እና ቁርጠኝነት ማሳያ የሆነው ይህ አለማቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ የሳይበር ደህንነት፣ ሰው ሰራሽ አስተውህሎት (AI)፣ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ (FinTech)፣ ስማርት ከተሞች፣ ስታርታፖች እና የቴክኖሎጂ ክህሎት ባሉ ወሳኝ ዘርፎች ላይ ያተኮረ ነው።
ከግንቦት 8 እስከ ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል በሚካሄደው ኤክስፖ በዘርፉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ በሚካሄዱ የውይይት መድረኮች ከመላው ዓለም የተውጣጡ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች፣ የፖሊሲ አውጭዎች፣ ተመራማሪዎች፣ የዘርፉ መሪዎችና ምሁራን በስፋት በመሳተፍ ላይ ናቸው።
በኤክስፖው በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጡ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና ድርጅቶችን እንዲሁም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራሮችን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊወች ጎብኝተውታል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments