
"አካታች ያልሆነ ቴክኖሎጂ ዓላማ እንደሌለው ጥረት ነው" ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
"አካታች ያልሆነ ቴክኖሎጂ ዓላማ እንደሌለው ጥረት ነው" ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለአፍሪካ ትብብር እና ብልፅግና በሚል መሪ ቃል የሚደረገውን የኢቴክስ ሁለተኛ ቀን ውሎ በንግግር ከፍተዋል።
ክቡር ጠ/ሚኒስትሩ በንግግራቸው ኤ.አይ ህልም ሳይሆን የሴክተሮች አንቀሳቃሽ ሞተር ነው ያሉ ሲሆን አፍሪካ አጋዠ የሆኑ ፖሊሲዎችን እና በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሀይልን በማቀናጀት ችግሮቿን መፍታት ይገባታል ብለዋል።
የዳታ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ እንደ አህጉር የቴክኖሎጂ ነፃነታችንን የምናረጋግጥበት አንዱ መንገድ በመሆኑ በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑን ክቡር ጠ/ሚንስትሩ አፅንኦት ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ ከ5 ዓመታት በፊት በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ፈር ቀዳጅ ሊያደርጋት የሚችለውን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አቋቁማ ወደ ስራ ገብታለች። ኢንስቲትዩቱ አፍሪካ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ተጠቃሚና ተከታይ ብቻ ሳትሆን በዘርፉ ተፅዕኖ ፈጣሪ ለመሆን አጋዥ ነው።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments