የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖ...

image description
- In Technology Trends    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የሚሳተፍበት አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ በመካሄድ ላይ ነዉ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የሚሳተፍበት አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ በመካሄድ ላይ ነዉ።

*******************

ITDB ግንቦት 8/2017፦ከ10 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የሚታደሙበትና በምስራቅ አፍሪካ ቅልቁ አለምአቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነዉ።

ETEX 2025 ኤክስፖ ከአዳዲስ ቴክኖሎጂ አቅርቦት ጋር ተያይዞ በአለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያተረፉ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ሲሆን

በኤክስፖው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጨምሮ የአገር ውስጥና አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ከማስተዋወቅ ባለፈ የተለያዩ የፓናል ውይይቶች ይካሄዳሉ።

በኤክስፖው ከፍተኛ ተቀባይነትና ዕውቅና ያላቸው ከመቶ በላይ የአገር ውስጥና የውጭ የቴክኖሎጂ አቅራቢዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ያስተዋውቃሉ።

ኤክስፖውን ያዘጋጁት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርና የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሳይበር ደህንነት ተቋም ጋር በመተባበር ነው።

ስማርቲ ሲቲ፣የሳይበር ደህንነት፣አርቴፊሻል ኢንተለጀንስና ዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ ውይይቶችን ጨምሮ የሮቦቲክስና ሌሎች የቴክኖሎጂ ውድድሮች የሚካሄዱበት ነው።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments