
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አማካኝነት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤትን በቴክኖሎጂ ለማዘመንና ምቹ የስራ ከባቢን መፍጠር የሚያስችል ፕሮጀክት ተግባራዊ ተደርጎዋል
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አማካኝነት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤትን በቴክኖሎጂ ለማዘመንና ምቹ የስራ ከባቢን መፍጠር የሚያስችል ፕሮጀክት ተግባራዊ ተደርጎዋል
***************
ITDB፦ ሚያዝያ 16/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ በማድረግ መቹ የሆነች ዘላቂ ችግሮችን መቋቋም የምትችል ከተማ ለመገንባት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እየፈፀመ ይገኛል። በመሆኑም ከሚፈፅማቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት መካከል አንዱ ለተቋማት ምቹ የስራ ከባቢን በመፍጠር በቴክኖሎጂ ማስታጠቅና ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥን መፍጠር መቻል ነዉ።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በቴክኖሎጂ በማዘመንና ምቹ የስራ ከባቢን መፍጠር የሚያስችል ፕሮጀክቶች በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አማካኝነት በአጭር ግዜ ዉስጥ ተግባራዊ ተደርጎዋል። በዚህም መሰረት በዛሬው ዕለት የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድና ስትራቴጂክ ካዉንስል አባላት እንዲሁም የመሬትና ግንባታ ጉዳዬች ቋሚ ኮሚቴ ስብሳቢ ዶ/ር አቶሜ አበበና የምክር ቤቱ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ምቹ ከባቢን ከመፍጠርና በቴክኖሎጂ ከማዘመን አንፃር የተከናወነው ተግባራት በዝርዝር ተዳሰዋል።
በተከናወኑ ዝርዝር ተግባራት ላይ መሰረት ያደረገ ሀሳብ እና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን ከነዚህም መካከል ቢሮዉን ከማዘመን ባሻገር ወረቀት አልባ አገልሎቶችን መስጠት የሚስችሉ ዘርፎችን የመለየት ስራ መሰራቱንና አገልግሎቱን ፈጣንና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ መስጠት የሚያስችል ስማርት ኦፊስ ትግበራን እንደሚሹና ተቋሙን ለማዘመን የተሰሩ ስራዎች በማጠናቀቅ ቴክኖሎጂን በተገቢዉ መንገድ ከማላመድ አንፃር ለተቋሙ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንደሚያስፈልግ የምክር ቤቱ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች አመላክተዋል።
በመጨረሻም የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ ቀሪ ስራዎች በአጭር ግዜ ዉስጥ እንደሚጠናቀቁና ስማርት ኦፊስ ትግበራዉን በተመለከተ ከሁለቱም ተቋማት ቴክኒካል ኮሚቴ በማዋቀር በአጭር ግዜ ዉስጥ ወደ ስራ እንደሚገባ አመላክተዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments