
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት እና የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጄንሲ አመራሮች በተገኙበት የካዳስተር ሲስተም የደረሰበትን ደረጃ ገመገሙ
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት እና የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጄንሲ አመራሮች በተገኙበት የካዳስተር ሲስተም የደረሰበትን ደረጃ ገመገሙ
******************
ITDB፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ለመሬት ይዞታ ምዝገባና መሬጃ ኤጄንሲ በኢንፎርሜሽን መረጃ መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) እየለማ ያለውን የካዳስተር ሲስተም የደረሰበትን ደረጃ ገምግሟል።
በግምገማ መድረኩም የኢኖ/ቴክ/ል/ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላትና የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጄንሲ አመራሮችና ስራውን ስከታተሉ የነበሩ ቴክኒካል ቡድን አባላትም የተገኙ ሲሆን የሲስተም ልማቱ የደረሰበትን ደረጃ አልሚው ድርጅት የሆነው የኢንፎርሜሽን መረጃ መረብ ደህንነት አስተዳደር ባለሙያዎች በዝርዝር ለአመራሮቹ አቅርበዋል።
በቀረበውም የካዳስተር ሲስተም ልማት ደረጃ ላይ ባለፎ ሚያዚያ 09/2017 ዓ/ም በሸገር ከተማ አስተዳደር በኮዬ-ፌጬ ክ/ከተማ በመገኘት ሲስተሙ በተግባር ያለበትን ሁኔታ በመስክ የተመለከተው የሁለቱም ተቋማት አመራሮች በአካል የተመለከቱትን መስተካከል ያለባቸውን ጉዳዮች ጨምሮ በአጠቃላይ አሁንም ሲስተሙ ማካተት ያለባቸውን ነጥቦች በዝርዝር በማንሳት ስራው ከሚፈለገው ፍጥነት አኳያ መሔድ እንዳለበት አሳስበዋል። በመጨረሻም ለስራው የኢንሳ ባለሙያዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት 7/24 የስራ መርህን በመጠቀም በሚፈለገው የጥራትና የብቃት ደረጃ መካተት ያለባቸውን ፍላጎቶችን (Requirements) በማካተት እንዲሰራ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አዋሌ ሞሐመድ የስራ መመሪያና አቅጣጫ በመስጠት አጀንዳው ተቋጭቷል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments