የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስትራቴጂክ ካዉ...

image description
- In Technology Trends    0

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስትራቴጂክ ካዉንስል አባላት በሸገር ከተማ አስተዳደር ኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ሀገር አቀፍ ካዳስተር ሲስተም ትግበራን ምልከታ አካሄዱ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስትራቴጂክ ካዉንስል አባላት በሸገር ከተማ አስተዳደር ኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ሀገር አቀፍ ካዳስተር ሲስተም ትግበራን ምልከታ አካሄዱ።

******************

ITDB፦ ሚያዝያ 9/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከINSA ጋር በጋራ በመሆን ወደ ስራ ያስገባው ሀገር አቀፍ ካዳስተር ሲስተም ትግበራን በሸገር ከተማ አስተዳደር ኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ካዳስተር ጽ/ቤት በመነኘት የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድና ስትራቴጂክ ካዉንስል አባላት የመስክ ምልከታ አካሄዱ።

በምልከታዉም ሲስተሙ ደህንነቱ የተጠበቀ ፈጣንና ቀልጣፋ የተቀናጀ አገልግሎት አሰጣጥን በኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ዲስትሪክት እየሰጠ መሆኑንና የመረጃ ትክክለኛነት በማረጋገጥ ካርታን ፕሪንት እስከ ማድረግ

የሚያስችል መሆኑ ተገልፆዋል። በተያያዘም በቀጣይ

ኢ-ላንዲንግ ላይ ትኩረት ያደረገ የመስክ ምልከታ የሚደረግ ይሆናል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments