
ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ለአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ Integrated culture, Arts , tourism management system ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስች ቅድመ ዝግጅት ተጠናቀቀ
ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ለአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ Integrated culture, Arts , tourism management system ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስች ቅድመ ዝግጅት ተጠናቀቀ
***********
ITDB፦ሚያዝያ 02/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ለአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ዘመኑን የዋጀ የቴክኖሎጂ አሰራር ስርአት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል 95% ከሰዉ ንክኪ ነፃ የሆነ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ፍትሐዊ የአሰራር ስርዓት የሚዘረጋ Integrated Culture, Arts and Tourism Management System ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራ አጠናቀቀ።
የቢሮውን የውስጥ አስራር በቴክኖሎጂ የተደገፈ በማድረግ አገልግሎት አሰጣጥን የሚያሻሽል የተለያየ የቋንቋ አማራጭ በማቅረብ በተገልጋዮ ዘንድ ሊፈጠሩ ለሚችሉ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችል ቻት ቡት ያለዉ እንዲሁም በኢትዮጵያና ግሪጎርያን ቀን አቆጣጠር መጠቀም የሚያስችል Integrated Culture, Arts and Tourism Management System System ለመዘርጋት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አዋሌ መሀመድ እና የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳው እንዲሁም የቢሮ ስትራቴጂክ ካዉንስል አባላት በተገኙበት ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከጉባ ቴክኖሎጂስ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል ።
ሲስተሙን በተመለከተ ዝርዝር ማብራርያ የተሰጠ ሲሆን በተሰጠዉ ማብራርያዉ ላይ መሰረት ያደረጉ ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄዎች ተነስተዋል። የተነሱትን ሀሳብ አስተያየቶች እንደግብዓት በመዉሰድ ምላሽ የተሰጠባቸዉ ሲሆን በመጨረሻም የሁለቱም ቢሮዎች ማኔጅመንት አባላት በቢሮው የተከናወኑ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን ተዘዋውረው ምልከታ አድርገዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments