በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖ...

image description
- In Technology Trends    0

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አማካኝነት ወደ ስራ የገባዉ E-School እና SchoolNet ትግበራ የመስክ ምልከታ ተካሄደ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አማካኝነት ወደ ስራ የገባዉ E-School እና SchoolNet ትግበራ የመስክ ምልከታ ተካሄደ

***********

ITDB፦ሚያዝያ 2/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አማካኝነት ወደ ስራ የገባዉና ከተማችን በትምህርቱ መስክ የሰለጠነ እና የተማረ የሰው ሃይል ከማፍራት አንጻር የጎላ አበርክቶ ያለዉ School Net እና E-School ትግበራ ምን ላይ እንዳለ በካራሎ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድና ስትራቴጂክ ካዉንስል አባላት በጋራ በመሆን የመስክ ምልከታ ተካሄደ፡፡

በዚህ ፕሮጀክት ትምህርት ቤቶቹ የመሰረተ ልማት ተጠቃሚነት ከፍ በማድረግ 3135 የቀንና የማታ ተማሪዎች መመዝገብ ያስቻለና መማር ማስተማሩ ሂደት እየተከናወነበት ያለ መሆኑን እንዲሁም ለተማሪዎች እና መምህራን በትምህርቱ ዘርፍ የተሻለ ጥራቱን የጠበቀ፣ ዘመናዊ እና ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተጠቁሟል። ከዚህም ባሻገር የፕላዝማና የሬድዮ ፕሮግራሞች ያመለጧቸዉ ተማሪዎች በይነ መረብን በመጠቀም በተመቻቸዉ ጊዜ እና ቦታ ላይ ማግኘት እንደሚያስችላቸው ተገልፆዋል።

ይህ ፕሮጀክት በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙትን 74 ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ተጠቃሚ ያደረገ እና የትምህርት ቤቶችን የኔትዎርክ መሰረተ ልማት Topology በመቀየር የሚሰራ እንዲሁም በውጤቱም ተማሪዎች፣ መምህራን እና የከተማው ማህበረሰብ እጅጉን ተጠቃሚ እና ቀጣይ ትውልድም በቅብብሎሽ እያሳደገው ሊሄድበት የሚችል ስራ ነው።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714

www.aaitdb.gov.et (https://www.aaitdb.gov.et/)

ITDB | Home Page

Addis Ababa City Innovation and Technology Development Bureau (ITDB) is a government organization that was originally constituted as an agency in April 2009 GC under proclamation No. 11/2009.


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments