
Addis Ababa ITDB - Innovation and Technology Development Bureau
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የ9ወራት ከተቋማት ጋር በቅንጅት የተሰሩ ስራዎች ተገመገመ
***
ITDB፦ሚያዝያ 15/2017 ዓ.ም
በ2017 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት ዉስጥ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተሰሩ ስራዎችና በመልካም አስተዳደር አገልግሎት አሰጣጥ የተሰሩ ስራዎችን የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድና ስትራቴጂክ ካዉንስል አባላት፣ ከስምንት ተቋማት የመጡ ተወካዬች እንዲሁም ከከንቲባ ጽ/ቤት የመጡ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ግምገማ ተካሄደ።
በ2017 በጀት ዓመት ከቢሮዉ ጋር በቅንጅት እንዲሰሩ የተለዩ 8 ተቋማትን በመለየት የቅንጅታዊ አሰራር የትስስር ሰነዱ ላይ ግልጽነት በመፍጠር እና የጋራ እቅድ በማቀድ ወደ ስራ መገባቱ ይታወሳል።
በመሆኑም የትስስሩ አጠቃላይ ዓላማ በበጀት ዓመቱ በእቅድ ትግበራ ሂደት ቢሮዉ ብቻውን ማሳካት በማይችላቸው ተግባራት ላይ ሴክተር ተቋማትን በመለየትና ስምምነት በመፍጠር ቢሮዉ የተሰጠውን ተልዕኮ በውጤታማነት ለማሳካት ነው፡፡
በበጀት ዓመቱ በ9 ወራት ዉስጥ በቅንጅት የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት የቢሮ ሪፎርም ዳሬክተር አቶ ግርማ ከበደ ያቀረብ ሲሆን በሪፖርቱም፦ የትስስሩ መርሆዎች፣ የተሰሩ ዋና ዋና ተግባራት፣ አማካይ አፈፃፀም፣ ጠንካራ ጎን፣ በድክመት የታዩ፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሔ ሀሳቦች፣ የተቋማት አፈፃፀም ደረጃ ከነዉጤታቸዉ በዝርዝር ዳሰዋል።
በተያያዘም የቀረበዉን ሪፖርት ላይ መሰረት ያደረገ ሀሳብ አስተያየት ከተሳታፊዎች የተነሱ ሲሆን የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ የተነሱ ሀሳብ አስተያየቶች ላይ ምላሽ በመስጠት ያለፉት ዘጠኝ ወራት የነበሩ ጥንካሬዎች ማስቀጠልና ክፍተቶችን ማረም እንደሚገባ አመላክተዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments