
Addis Ababa ITDB - Innovation and Technology Development Bureau
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት የቤቶች ጫረታ ሲስተም የደረሰበትን ደረጃ ገመገሙ
*******
ITDB፦ ሚያዚያ 13/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ተገንብተው ለአገልግሎት ዝግጁ የሆኑ የንግድ ቤቶች፣ ሱቆችንና የፓርኪንግ ቦታዎችን በግልጽ ጫረታ ለማከራዬት የሚያስችል ሲስተም በውስጥ አቅም ለምቶ ወደ ተግባር እንዲገባ ለማድረግ ቴክኒካል ቡድን አዋቅሮ ስምሪት በመስጠት የበአል ቀናትንና የእረፍት ቀናትን በመጠቀም በአስቸኳይ ቀደ ስራ እንዲገቡ አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወቃል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ የተዋቀረው ቴክኒካል ቡድን ከዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮና ከቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በቀረበለት ፍላጎት መግለጫ (Bussiness Requirement) መሰረት ከስራው አስቸኳይነት አኳያ የበአል ቀናትን ጨምሮ በመጠቀም ደረጃውን የጠበቀ የጫረታ ሲስተም ሲያለሙ መቆየታቸውን አንስተው የሲስተም ልማቱ የደረሰበትን ደረጃ ለስትራቴጂክ ካውንስል አባላት በቢሮው የስትራቴጂክ ካውንስል አዳራሽ በዝርዝር አቅርበዋል።
በቀረበውም ሲስተም ላይ ዝርዝር ቴክኒካል አስተያየቶች ማለትም የክፊያ ጉዳይ፣ የሠነዶች ቁጥጥርና ሌሎች ዝርዝር ቴክኒካል አስተያየቶች ተሰጥተውበት ቴክኒካል ቡድኑም የተሰጡትን አስተያየቶች በማካተት የሲስተም ልማቱ በፍጥነት ተጠናቆ ወደ ተግባር እንዲገባ የቢሮው ኃላፊ ክቡር አቶ አዋሌ ሞሐመድ የስራ መመሪያና አቅጣጫ በማስቀመጥ አጀንዳው ተቋጭቷል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments