
የተቋማችንን ስኬት ለማረጋገጥ ምን ማድረግ አለብን በሚል ርዕስ ዉይይት ተካሄደ
የተቋማችንን ስኬት ለማረጋገጥ ምን ማድረግ አለብን በሚል ርዕስ ዉይይት ተካሄደ
*****
ITDB፦መጋቢት 29/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራር እና ሰራተኞች የተቋማችንን ስኬት ለማረጋገጥ ምን ማድረግ አለብን በሚል ርዕስ ዉይይት ተካሄደ። በዉይይቱም ከከንቲባ ጽ/ቤት የመጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ የቢሮ አመራርና ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን መርሃ-ግብሩን የመሩት የቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊአቶ ግሩም አብተዉ የዉይይት መርሃ-ግብሩ ዓላማ አዳዲስ ከመጡ ዓመራሮች ጋር በመሆን ተቋሙ የተሰጠዉን ተግባርና ሀላፊነት በአግባብ ለመወጣት መሰረታዊ የሆኑ መታረም የሚገባቸው ችግሮች ነቅሶ በማዉጣት የመፍትሔ ሀሳቦችን ማምጣት መሆኑን ገልፀዋል።
በመርሃ-ግብሩ አዲስ የመጡ ማለትም ቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ፣ ም/ቢሮ ሀላፊዎች አቶ ነብዩ ፍቃዱ እና አቶ ዳኛቸዉ ፈለቀ እራሳቸዉን ያስተዋወቁ ሲሆን የቢሮ ስማርት ሲቲ ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን የተቋሙን ስኬት ለማረጋገጥ ምን መደረግ አለበት በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ አቅርበዋል። ሰነዱም ስለ ስማርት ሲቲ ምንነት፣ ስለቢሮ አደረጃጀት፣ የአሰራር ስርዓት፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና የመፍትሔ ሀሳቦች ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥተዋል።
በተያያዘም የቢሮዉ ትራንስፎርሜሽን ሂደት የሚገኝበት ሁኔታ ላይ መሰረት በማድረግ የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ፣ ከከንቲባ ጽ/ቤት የመጡ ከፍተኛ የስራ አመራሮች አቶ ሞላ ሞገስ እና አቶ መኮንንን ያየ የቢሮ ሰራተኞችን ያወያዩ ሲሆን በዉይይቱም ከተነሱ ሀሳብ አስተያየቶች መካከል ለሰራተኛዉ የስራ ተነሳሽነትን ከመፍጠር አንፃር፣ በሁሉም እርከን የተናበበ ዕቅድ ከማቀድ አንፃር፣ ሚዲያና ኮምንኬሽን በተመለከተ፣ የመልካም አስተዳደር ችግርን በተመለከ ከተነሱ ሀሳቦች ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ ። በመሆኑም የተነሳዉ ሀሳብ አስተያየት እንደግብአት በመውሰድ ምላሽ የተሰጡበት ሲሆን ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ ማለትም ድጋፋፍና ክትትል የሚሹ ጉዳዬች ላይ ማተኮር እንደሚገባ፣ ጠንካራ የሆነ የግምገማ ሰርዓት መዘረጋት፣ ስነምግባርን የተላበሰ ሰራተኛ ማፍራት ላይ ትኩረት አድርጎ መስራትና በየጊዜዉ የአቅም ግንባታ መድረኮችን ማዘጋጀት ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments