በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖ...

image description
- In project    0

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከINSA ጋር በመሆን እያለማ ያለው (CRPRS) ወይም ካዳስተር ሲስተም የደረሰበት ደረጃ ተገመገመ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከINSA ጋር በመሆን እያለማ ያለው (CRPRS) ወይም ካዳስተር ሲስተም የደረሰበት ደረጃ ተገመገመ

*****************

ITDB፦ መጋቢት 2017 ዓም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከINSA ጋር በጋራ በመሆን እያለማ ያለው (CRPRS) ወይም ካዳስተር ሲስተም ተገመገመ።በግምገማውም የቢሮው አመራሮች፣ የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ እንዲሁም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት የተገኙ ሲሆን ሲስተሙን ከINSA በመጡ ባለሙያዎች ዝርዝር ማብራርያ ተሰጥቶበታል።

ሲስተሙ አምስት ዋና ዋና ሞጁሎች ማለትም RRPR, RECS, CDMT, CSM, OLSM ያሉትና ደህንነቱ የተጠበቀ ፈጣን እና ቀልጣፋ እንዲሁም የተቀናጀ አገልግሎት አሰጣጥን በአንድ ያቀፈ ሲሆን በቀረበው ዝርዝር ማብራርያ ላይ መሰረት ያደረገ ሃሳብ አስተያየት ተሰጥቷል። የተሰጡ ሃሳብ አስተያየቶችን እንደ ግብአት በመውሰድ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ለይቶ በማስቀመጥ መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments