የኦፕሬሽን እና አገልግሎት ዘርፍ ሀላፊዎች የስራ...

image description
- In project    0

የኦፕሬሽን እና አገልግሎት ዘርፍ ሀላፊዎች የስራ ርክክብ ተከናወነ።

የኦፕሬሽን እና አገልግሎት ዘርፍ ሀላፊዎች የስራ ርክክብ ተከናወነ።

**************

ITDB፦መጋቢት 22/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የኦፕሬሽን እና አገልግሎት ዘርፍ ሀላፊ በነበሩት አቶ ምህረቱ ደሳለኝና አዲስ በመጡት የዘርፉ ሀላፊ አቶ ዳኛቸው ፈለቀ መካከል የስራ ርክክብ ተደርጓል። በዚህም የርክክብ ስነ-ስርዓት ላይ የዘርፉ ዳይሬክተሮች የተገኙ ሲሆን ስለተከናወኑ ተግባራት እና ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች የዘርፉ ሀላፊ በነበሩት አቶ ምህረቱ ደሳለኝ ዝርዝር ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ክፍተቶች ካሉ በማረም ጥንካሬዎችን ማስቀጠል እንደሚገባ አመላክተዋል። በተያያዘ አዲስ የመጡት የኦፕሬሽን እና አገልግሎት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ዳኛቸው ፈለቀ ስራዎችን በጥሩ ሁኔታና በነበረዉ ጠንካራ መንፈስ ለማስቀጠል ቁርጠኛ እንደሆኑና ስለተደረገላቸው ዝርዝር ማብራሪያ እንዲሁም መልካም አቀባበል ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments