የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖ...

image description
- In project    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የአመራሮች ስራ ርክክብ ተከናወነ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የአመራሮች ስራ ርክክብ ተከናወነ

*************************

ኢቴልቢ መጋቢት 19/2017 ዓ/ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ በነበሩት በአቶ ሰለሞን አማረ እና አዲስ ተሹመው በመጡት የቢሮው ኃላፊ በአቶ አዋለ መሐመድ መካከል የስራ ርክክብ ተደርጓል።በዚህ የርክክብ ስነ ስርዓት ላይ የቢሮው ስማርት ሲቲ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁንና የቢሮው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግሩም አብተው እንዲሁም የቢሮው ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል።

መርሃ ግብሩን የመሩት አቶ ግሩም አብተው አዲሶቹን የአመራር አባላት እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ አሰስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አማረ ስለ ቢሮው አሁናዊ ሁኔታ ለአዲሶቹ የአመራር አባላት ገለፃ እንዲያደርጉ ጋብዘዋቸዋል፡፡

የቀድሞ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አማረ ቢሮው ከዚህ ቀደም የሰራቸውንና እየተሰሩ ያሉትን፣ጅምር ስራዎች ያሉበት ደረጃ እና ሁኔታ ላይ ገለፃ በማድረግ በቀጣይ መከናወን ባለባቸዉ ተግባራት ላይ ምክረ ሃሳብ ሰጥተዋል። ቢሮው እየሰራ ያለውን በጎ ስራ በተመለከተ በቄርቆስ ክ/ክፍለ ከተማ ለ12 አቅመ ደካማ አባ ወራዎች የተጀመረውን መኖሪያ ቤት ያለበትን ሁኔታ እና በመግለፅ ጅምሩን ማስጨረስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክረ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።

የቀድሞ የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ እንዲሁም ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ የማነ ደሳለኝ በበኩላቸው አዲስ ለመጡት አመራሮች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈው ለተተኪዎቹ የአመራር አባላት ማንኛውንም መረጃ መስጠት የሚችሉ እና ተባባሪ የሆኑ ሰራተኞች መኖራቸውን ገልጸው መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተውላቸዋል።

አዲሱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አዋሌ መሐመድ ራሳቸውን በሰፊው ካስተዋወቁ በኃላ በእንድ መንፈስ ተግባብተንና ተስማምተን ከሰራን ዓላማችንን ከግብ ማድረስ እንደሚቻልና ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር በጥሩ የስራ መንፈስ ጥሩ ዉጤት ማምጣት እንደሚጠበቅ እና ለዚህም ራሳችንን ማዘመን አለብን ሲሉ ሀሳባቸዉን ገልፀዋል። የቀድሞ የቢሮ ሀላፊ አቶ ሰለሞን አማረንም ለሳዩዋቸው መልካም አቀባበል እና ቀና ትብብር አመስግነዋቸዋል።

በተያያዘም የስማርት ሲቲ ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን በበኩላቸው አሁን ያለው ለውጥ አዲስ ጉልበት እንደሚያመጣ መታሰብ እንዳለበት እና የሚሄዱትም ከኛ ጋር መሆናቸውንና በየትኛም መንገድ የትም ብንሄድ ዋና ዓላማችን ከተማችንን የማሳደግ እና የማዘመን ሀላፊነት አንግበን መሆን እንደሚገባ አመላክተዋል።

በመጨረሻም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ነብዩ ፍቃዱ የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኦፕሬሽን እና አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ፈለቀ እራሳቸውን ለቢሮው ሰራተኞች አስተዋውቀዋል። በተጨማሪም የቢሮ የየዘርፉ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች ራሳቸውን አዲስ ለመጡት ኃላፊዎች ያስተዋወቁ ሲሆን ወደ ሌላ ስፍራ ለሚሄዱት የቀድሞ ኃላፊዎች መልካም የስራ ግዜ የተመኙ ሲሆን በቢሮው አዲስ ለተሾሙት ኃላፊዎች መልካም የስራ ዘመን በመመኘት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments