
ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሰራተኞች የሰዉ ሀይል ስምሪት በልዩ ሁኔታ ለማመጣጠን በወጣ የዝዉዉር ምደባ ደንብ ላይ ገለፃ ተደረገ።
ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሰራተኞች የሰዉ ሀይል ስምሪት በልዩ ሁኔታ ለማመጣጠን በወጣ የዝዉዉር ምደባ ደንብ ላይ ገለፃ ተደረገ።
**************
ITDB፦ መጋቢት 17/2017 ዓ.ም
የአፈፃፀም ክፍተት እና የመልካም አስተዳደር ችግር ለመቅረፍ የተመጣጠነ የሰው ሀይል እንዲኖር በማድረግ ጥራት ያለዉ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥራን እና ሰራተኞችን በማገናኘት የተቋማት ዉጤታማነት ማሳደግ በማስፈለጉ ከስልሳ ፐርሰንት በላይ የሰው ሀይል ከተሟላላቸዉ ላይ ዝቅተኛ የሰዉ ሀይል ቁጥር ወዳላቸው የመንግስት መስርያ ቤቶች በልዩ ሁኔታ በማዛወር ወይም በመመደብ የተሻለ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር በማስቻል የተገልጋዩን እርካታ ከፍ ማድረግ በመፈለጉ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሰራተኞች ደንብ ቁጥር 179/2017 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት መስርያ ቤቶች የሰዉ ሀይል ስምሪት በልዩ ሁኔታ ለማመጣጠን የወጣ የዝውውርና ምደባ ደንብ ላይ መሰረት ያደረገ ገለፃ ተደርጓል።
የገለፃውን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት መስርያ ቤቶች የሚስተዋለዉን አለመመጣጠን ሊፈታ የሚችል የማመጣጠን ዝውውር ምደባ ደንብ ላይ ዝርዝር ማብራሪያ እንደሚሰጥና ቢሮው ባቋቋመው ኮሚቴ መሰረት ከማዕከል፣ ክ/ከተማና ወረዳ ባሉ ተዋረዶች የማመጣጠን ስራእንደሚሰራ ገልፀዉ የቢሮ ሰራተኞች ይህንን ታሳቢ በማድረግ መስጠት የሚገባው መረጃዎች በመስጠት መተባበር እንደሚገባ በማመላከት መርሃ-ግብሩን በይፊ አስጀምረዋል።
ደንብ ቁጥር 179/2017 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት መስርያ ቤቶች የሰው ሀይል ስምሪት በልዩ ሁኔታ ለማመጣጠን የወጣ የዝውውርና ምደባ ደንብ ላይ የተዘጋጀውን ሰነድ ያቀረቡት የቢሮ ሰዉ ሀብት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሪት ፀሀይ በዳዳ ጠቅላላ ድንጋጌ፣ የተፈፃሚነት ወሰን፣ ስለዝዉዉር ምደባ አፈፃፀም፣ የልዩ ዝዉዉር ምደባ ኮሚቴ ተግባርና ሀላፊነት፣ በዝውውር አፈፃፀም የሰራተኛው መብትና ግዴታ እና የተከለከሉ ተግባራት ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ስጥተዋል።
በመጨረሻም በቀረበው ሰነድ ላይ መሰረት ያደረገ ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄ ከቢሮ ሰራተኞች የቀረበ ሲሆን የቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ እና ሰዉ ሀብት ዳሬክተር ምላሽ ሰጥተዉበታል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments