
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የፖለቲካ አዝማሚያ ትንተና ሲስተም (PTAS) የአሰልጣኞች ስልጠናን ተሰጠ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የፖለቲካ አዝማሚያ ትንተና ሲስተም (PTAS) የአሰልጣኞች ስልጠናን ተሰጠ
****************
ITDB፦ መጋቢት 2017ዓ/ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የፖለቲካ አዝማሚያ ትንተና ሲስተም የአሰልጣኞች ስልጠናን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ተሰጥል፡፡
በስልጠናው ላይ የአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ም/ል ሃላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁንን ጨምሮ የ11ዱም ክፍለ ከተማ የዘርፍ አመራሮች፣ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ፣ የሚመለከታቸው አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዉበታል፡፡
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ለምቶ በከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ተገምግሞ ለአገልግሎት እንዲውል ፈቃድ የተሰጠው የፖለቲካ አዝማሚያ ትንተና ሲስተም ስርዓት በጊዜ ሂደት ሃሳብና አስተያየቶችን በመለየት፣ ለመከታተልና ለመተንተን ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው በስልጠናው ላይ ተገልፆል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ቱሉ ጥላሁን የሲስተሙ በህዝብ አስተያየት፣ በፖለቲካ እንቅስቃሴዎች እና የፖለቲካ መልከዓ ምድሮች ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን በአከባቢያዊ ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ለመዘገብ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አክለውም ሲስተሙ የለማበት ዓላማ የፖለቲካ አዝማሚያዎችን በማህበራዊ ሚዲያ፣ የዜና ማሰራጫዎች፣ የህዝብ አስተያየት መስጫና የመንግስት ሪፖርቶች ካሉ ምንጮቹ ለመሰብሰብና ለማስኬድ ማዕድ የተፈጥሮ ቋንቋ ማቀነባበሪያ (NLP) ባግባቡ ለመጠቀም ያስችላል ብለዋል፡፡
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ጥላሁን አረጋ በበኩላቸው በሲስተሙ የመረጃ ፍሰትን ከምንጩ ለማወቅ፣ ወጥ ለማድረግ፣ ታማኝ መረጃን ለማግኘት እንዲሁም የሚከናወኑ ስራዎች ፈጣንና ውጤታማ ለማድረግ እንደሚረዳ ገልፀዋል፡፡ አክለውም ያሰራር ስርዓትን ፈጣንና ቀልጣፋ በማድረግ ተለዋዋጭ ሆኖ በተፈለገው መጠንና ልክ ጥቅም ላይ እንዲውል ስልጠናዎች እና የተጠቃሚው ህብረተሰብ አስተያቶች አስፈላጊ መሆናቸውን አንስተዉ የሲስተሙን አገልግሎት በክፍለ ከተማ በፍጥነት በማስጀመር ተግበሩ እየተለካ እንደሚሄድ ተመላክተዋል፡፡ በቀጣይነትም ስልጠናው በየክፍለ ከተማው ላሉት ወረዳዎች የሚሰጥ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments