
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የለማዉ ኢ-ስኩል ሲስተም እና ስኩል-ኔት ኦፕቲማይዜሽን ፕሮጀክቶች የተከናወኑ ተግባራት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተገመገሙ።
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የለማዉ ኢ-ስኩል ሲስተም እና ስኩል-ኔት ኦፕቲማይዜሽን ፕሮጀክቶች የተከናወኑ ተግባራት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተገመገሙ።
***************
ITDB፦ መጋቢት 15/2017 ዓ.ም
በመርሃ-ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አማረ ፣ የትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱና በሁለቱ ቢሮ ዘርፉን የሚመሩ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል።
የኢ-ስኩል ሲስተም በ11 ሞጁሎች የተካተቱ 153 ዋና ዋና ተግባራትን የያዘ ሲስተም መሆኑን እና በሲስተሙ አማካይነት በየትምህርት ቤቱ ተማሪዎችን ኦን ላይን ከመመዝገብ ጀምሮ የትምህርት ተቋማትን አጠቃላይ መረጃዎች ወደ ሲስተም የማስገባት ስራ መሰራቱን የተገለፀ ሲሆን ከስኩል ኔት ኦፕቲማይዜሽን ስራ ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል ፕሮጀክቱ ተግባራዊ በተደረገባቸው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመገኘት መሰረተ ልማቶችን የመጠገን እና ሙሉ ለሙሉ የተበላሹትን በአዳዲስ የመቀየር ተግባር መከናወኑን በቀረበ ሪፖርት ተገልጿል።
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አማረ በኢስኩል ሲስተም በተካተቱ ሞጁሎች ውስጥ የሚገኙ ተግባራት በአግባቡ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ቀሪ ስራዎችን በማጠናቀቅ በአጭር ጊዜ ሲስተሙን ወደ ስራ ማስገባት እንደሚገባ አመላክተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የኢስኩል ሲስተም በየትምህርት ተቋማቱ በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን ቢሮው ከሲስተሙ አተገባበርና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተገናኘ ለመምህራንን እና የአይ ሲቲ ባለሙያዎች እንዲሁም ለሌሎች ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ስልጠና መሰጠቱን እና ከስኩል ኔት ኦፕቲማይዜሽን ስራው ጋር በተገናኘም መሰረተ ልማቶቹ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ቢሮው ድጋፍና ክትትል በማድረግ ላይ መሆኑን ገልጸው ከተማ አስተዳደሩ ለፕሮጀክቶቹ ተግባራዊነት ከፍተኛ ወጪ ማውጣቱን በመጥቀስ ቀሪ ስራዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ሙሉ ለሙሉ ወደ አገልግሎት ማስገባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በመጨረሻም በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊዎች የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን ከነዚህም መካከል በከተማ ደረጃ የሚያኮራና ትልቅ ሲስተም እንደሆነና ነገሮች በጥሩ ሁኔታ እየተከናወኑ መሆኑን እንዲሁም በጋራ መታየት ያለባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ያመላከቱ ሲሆን ሲስተሙ ከሞላ ጎደል የተጠናቀቀ በመሆኑ ወደ ስራ በማስገባት የማላመድና የጎደሉትን የማሟላት ስራ ሊከናወን እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments