የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የሃብት ብክነት...

image description
- In Technology Trends    0

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የሃብት ብክነትን ለመከላከል እየሰራ ይገኛል

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የሃብት ብክነትን ለመከላከል እየሰራ ይገኛል

****************

ITDB፦መጋቢት 10/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ጠግኖ ወደ ስራ የማስገባት ስራ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እና የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ጋር በጋራ በመሆን ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን በመጠገን ከ70 ሚሊየን ብር በላይ የመንግስት ወጪ ማዳን ተችሏለል።

ጥገና እየተከናወነባቸው የሚገኙ ተግባረ ኢድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ቅኝት የተደረገባቸው ሲሆኑ መንግስትን ካላስፈላጊ ወጪ ለማዳን በርካታ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን የመጠገንና መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል የሚችሉትን በአግባቡ የመለየት ስራ እየተሰራ እንደሆነ የክፍለ ከተማው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት የአይ ቲ ባለ ሙያዎች ገልጸዋል። አክለውም በብልሽት ምክንያት ሊወገዱ የነበሩትን በጥገና መልሰው ጥቅም ላይ እንዲውሉ በማድረግ ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግሉ እና የመንግስትን አላስፈላጊ ወጪ የሚያስቀር መሆኑን አመላክተዋል።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት አቶ አብዩ በየነ በክፍለ ከተማው ባሉ 10 ወረዳዎች በሶስት ሳምንት ውስጥ በርካታ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን የመጠገን ስራ እየተሰራ መሆኑንና ከዚህም ባሻገር በፅ/ቤቱ ያሉ የአይ ቲ ባለሙያዎችን የዕውቀት አድማሳቸውንና ተሞክሮኣቸውን ከፍ እያደረጉ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የኦፕሬሽንና ጥገና ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ ድርሻዬ ካሳዬ በከተማ መስተዳደሩ ስር ባሉ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ በብልሽት ምክንያት ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ንብረቶችን በፍጥነት በመጠገን ጥቅም ላይ የሚውሉበትን አሰራር ቢሮ ዘርግቶ እየሰራ እንደሚገኝና እስካሁን በተከናወነው ተግባር መንግስት ሊያወጣ የነበረውን ከ70 ሚሊየን ብር በላይ መታደግ እንደተቻለ ገልፀዋል።

የተጀመረውን ስራ አጠናክሮ በማስቀጠል ጠቅላላ ስራው ሲጠናቀቅ ከዚህ በላይ ውጤት የሚጠበቅ ይሆናል። ይህም በተቋማት ስር የሚገኙ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ስርዓት ላይ ችግር ፈቺ ስራዎችን በመስራት የአገልግሎት አሰጣጡን ስርዓት የበለጠ ሊያጠናክር የሚችል ተግባር ነው።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments