
የተበላሹ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን በመጠገን ከ73 ሚሊየን ብር በላይ የመንግስት ወጪ ማዳን ተችሏል
የተበላሹ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን በመጠገን ከ73 ሚሊየን ብር በላይ የመንግስት ወጪ ማዳን ተችሏል
*********************
ITDB፦ መጋቢት 2017 ዓ.ም
የመርሃ ግብሩ ዓላማ በከተማ አስተዳደሩ ስር ባሉ የመንግስት ተቋማት ተበላሽተዉ የሚገኙ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እቃዎችን ተጠግነዉ ወደ ስራ ማስባት እና ሊጠገኑ የማይችሉትን በአግባቡ በማስወገድ የከተማ አስተዳደሩ ሊያወጣ የሚችለዉን አላስፈላጊ ወጪ ማዳን ሲሆን የስራዉ ወሰን በከተማ አስተዳደሩ ስር ባሉ 346 ተቋማት ማለትም በሴክተሮች፣ ሆስፒታሎች፣ ኮሌጆች፣ ክ/ከተሞችና 4603 ወረዳዎች ላይ ያሉ የተለያዩ ኤሌትሮኒክስ እቃዎች ናቸዉ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ጋር በመሆን የተጠገኑ፣ መለዋወጫ የሚፈልጉ እና የሚወገዱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማቴርያል በተመለከተ ሪፖርት ያቀረብት የኦፕሬሽንና ጥገና ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ ድርሻዬ ካሰኝ ሲሆኑ በሪፖርቱ የቡድን አወቃቀር፣ የግዜ ሰሌዳ፣ የየክ/ከተማዎች የስራ ክንዉን፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች እንዲሁም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫና በተሰራው ስራ ከዳነው 71 ሚሊየን ብር ውስጥ ከ3 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆነው የጥገና አገልግሎት ለሚሠጡ ባለሙያዎች የሚከፈል የነበረ ወጪ መሆኑ ጠቁመዋል::
በቀረበዉ ሪፖርት ላይ መሰረት ያደረጉ የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች ከተሳታፊዎች የተነሱ ሲሆን የቢሮ ሀላፊ፣ ም/ቢሮ ሀላፊ እና የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን የንብረት ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ ምላሽ ሰጥተዉበታል። በመጨረሻም ከማዕከል እስከ ወረዳ ባሉ የክ/ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤቶች ለጥገና የሚሆን ፕሮፌሽናል የኔትወርክ ቱል ኪት ቢሮዉ በስጦታ መልክ አበርክቷል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments