የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ጋር በጋራ በመሆን በተለያዩ የመንግስት ተቋማት ያሉ ብልሽት የገጠማቸው IT ማቴሪያሎች እና ኤሌትሮኒክስ እቃዎችን ጠግኖ መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ሂደት ላይ መሰረት ያደረገ ግምገማና ሪፖርት ተካሄደ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ጋር በጋራ በመሆን በተለያዩ የመንግስት ተቋማት ያሉ ብልሽት የገጠማቸው IT ማቴሪያሎች እና ኤሌትሮኒክስ እቃዎችን ጠግኖ መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ሂደት ላይ መሰረት ያደረገ ግምገማና ሪፖርት ተካሄደ
*********************
ITDB፦ መጋቢት 2017 ዓ.ም
የመርሃ ግብሩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሰለሞን አማረ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኦፕሬሽንና ጥገና አገልግሎት ዘርፍና ከመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ጋር የተሰሩ ስራዎች የምናይበትና የምንገመግምበት መርሃ-ግብር ላይ እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አሰተላፈዉ። ቢሮው አገልግሎቶችን ዲጅታል ከማድረግ አንፃር በርካታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑንና ከዚህም ባሻገር በኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ የተቋሙን ሰራተኞች ጨምሮ ከ126ሺህ በላይ ሰዎች ተሳታፊ እንዲሆኑ ከቢሮ ባሻገር የክ/ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊዎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸዉን ገልፀዋል። አክለዉም የመንግስት ተቋማት ላይ የሚሰሩ ሰራተኞችን በቴክኖሎጂ ከማብቃት አንፃር ቢያስ አንዱን ቢቻል አራቱንም ኮርሶች መዉሰድ እንደሚጠበቅባቸው አመላክተዋል። በተያያዘም ቢሮው ከመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ጋር በመሆን አንድ ወር ባልሞላ ግዜ ዉስጥ ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ IT ማቴርያሎች ጠግኖ ወደ ስራ ማስገባትና በኦኘሬሽንና ጥገና አገልግሎት ዘርፍ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመማመላከት መርሃ-ግብር በይፋ አስጀምረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ምህረቱ ደሳለኝ ቢሮዉ የስምንት አመት ስማርት ሲቲ ስትራቴጂ ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንና ከነዚህም ተግባራት መካከል መንግስት የሚያወጣውን ወጪ በመታደግ ከተማዋን ከፍ የማድረግ ስራ እየተሰራ በመሆኑ ይህም ተግባር ከመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ጋር በመሆን ሁሉም ሴክተር ተቋማት የሚገለገሉበት ፕላት ፎርም ተዘርግቶ ወደ ስራ መገባቱን ገልፀዋል። አያይዘውም ንብረቶች ከመወገዳቸዉ በፊት በሶስት ፈርጆች ማለትም ተጠግነዉ ወደ ስራ የሚገብትን መለየት፣ መለዋወጫ የሚፈልጉትን እና በሁለቱም መንገድ የማይሆኑትን በአግባቡ የማስወገድ ስራ እየተሰራ መሆኑንና ከዚህም ባሻገር የሳይበር ደህንነት ተጋላጭነትን የሚቀነስበት ሁኔታ በመዘርጋት ከ71 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ IT ማቴሪያሎችን ማዳን መቻሉንና ለዚህም የክ/ከተማ IT ባለሙያዎች በጥብቅ ዲሲፕሊን ስራቸዉን እየሰሩ በመሆኑ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን የንብረት ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፀሀይ ደምሴ በመርሃ-ግብሩ ላይ በመገኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዉ ባለስልጣን መስርያቤቱ በ600 ተቋማት ዉስጥ ያሉ ቋሚና አላቂ ንብረቶች ባለስልጣን መስርያ ቤቱ በተቀመጠለት ተግባርና ሀላፊነት መሰረት በአግባቡ አገልግሎት ላይ መዋላቸውን መከታተል እና መቆጣጠር ስራ እንደሚሰራና ከዚህም ጋር በተያያዘ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አማካኝነት ሀሴት ማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተም ለምቶ ወደ ስራ በመገባቱ በቀላሉ ማየትና መከታተል መቻሉንና ከዚህም ባሻገር ኤሌትሮኒክስና ፈርኒቸር ስታንዳርዳይዜሽን የምናስተዳድርበት ስርዓት የመዘርጋት ሂደት ላይ መሆኑን ገልፀዉ ይህ መድረክ ንብረቶችን ጠግኖ መልሶ ስራ ላይ የማዋል ባህላችን በማሳደግ የመንግስን ሀብት የምናድንበት፤ የኔነት ስሜት የምንፈጥርበት መድረክ መሆኑንና ባለስልጣን መስርያ ቤቱ ከመጠገን ባሻነር ከፋይናንስ ቢሮ ጋር በመሆን ሌላ ግዥ እንዳይፈፀምና የግዢዉን ገንዘብ ለሌላ የልማት ስራ ላይ ማዋል መሆኑን በማመላከት በጥብቅ ዲሲፕሊንና በተደራጀ መልኩ በርካታ ስራዎች በመስራታቸዉ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments