
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አማካኝነት ወደ ስራ የገባዉ SchoolNet infrastructure optimization Project ትግበራ የመስክ ምልከታ ተካሄደ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አማካኝነት ወደ ስራ የገባዉ SchoolNet infrastructure optimization Project ትግበራ የመስክ ምልከታ ተካሄደ
******************
ITDB፦መጋቢት 5/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አማካኝነት ወደ ስራ የገባዉና ከተማችን በትምህርቱ መስክ የሰለጠነ እና የተማረ የሰው ሃይል ከማፍራት አንጻር የጎላ አበርክቶ ያለዉ SchoolNet infrastructure optimization Project ትግበራ በቦሌ ህብረተሰብ እና አሳይ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊና ም/ቢሮ ሀላፊዎች በተገኙበት የመስክ ምልከታ ተካሄደ፡፡
በዚህ ፕሮጀክት ትምህርት ቤቶቹ የመሰረተ ልማት ተጠቃሚነት ከፍ በማድረግ መማር ማስተማሩና የተማሪዎች ፈተና አሰጣጥ ያለምንም መቆራረጥ እየተከናወነ መሆኑንና ለተማሪዎች እና መምህራን በትምህርቱ ዘርፍ የተሻለ ጥራቱን የጠበቀ፣ ዘመናዊ እና ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተጠቁሟል።
ይህ ፕሮጀክት በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙትን 74 ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ተጠቃሚ ያደረገ እና የትምህርት ቤቶችን የኔትዎርክ መሰረተ ልማት Topology በመቀየር የሚሰራ እንዲሁም በውጤቱም ተማሪዎች፣ መምህራን እና የከተማው ማህበረሰብ እጅጉን ተጠቃሚ እና ቀጣይ ትውልድም በቅብብሎሽ እያሳደገው ሊሄድበት የሚችል ስራ ነው።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments