የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖ...

image description
- In Technology Trends    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የፖለቲካ አዝማሚያ ትንተና ሲስተም አለማ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የፖለቲካ አዝማሚያ ትንተና ሲስተም አለማ

********************

ITDB፦መጋቢት 4/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የለማ የፖለቲካ አዝማሚያ ትንተና ሲስተም የቢሮ ሀላፊና ም/ቢሮ ሀላፊዎች፣ የብልፅግና ፖርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አለማየሁ ዕጅጉ እንዲሁም ከፖርቲ ጽ/ቤት የመጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት የተገመገመ ሲሆን የፖለቲካ አዝማሚያ ትንተና ሲስተም ስርዓት በጊዜ ሂደት የፖለቲካ አዝማሚያዎችን ለመለየት፣ ለመከታተልና በመተንተን ላይ የተደገፈ ሲስተም ሲሆን ይህ ስርዓት በህዝብ አስተያየት፣ በፖለቲካ እንቅስቃሴዎች እና የፖለቲካ መልከዓ ምድሮች ተለዋዋጭ ለዉጦችን በአካባቢያዊ ሆነ በዓለም አቀፉ ደረጃ ለመመዝገብ ይረዳል።

ሲስተሙ የለማበት ዓላማ የፖለቲካ አዝማሚያዎች፣ ባህሪዎችንና የህዝብ ስሜት ስልታዊ በሆነ መንገድ መከታተል፣ መተንተን እና መተንበይ ሲሆን እንዲህ አይነቱ ስርዓት እንደ ማህበራዊ ሚዲያ፣ የዜና ማሰራጫዎች፣ የህዝብ አስተያየት መስጫ እና የመንግስት ሪፖርቶች ካሉ ምንጮቹ ለመሰብሰብ እና ለማስኬድ በተለምዶ የመረጃ ማዕድን፣ የተፈጥሮ ቋንቋ ማቀነባበሪያ (NLP) ይጠቅማል።

ሲስተሙ የመረጃ ፍሰት ትንተና ሂደት በማዕከል እና ክ/ከተማ ደረጃ ያለዉና በሲስተሙ ስለሚከናወኑ ተግባራት፣ የሚሰጠዉ ጥቅም፣ ነባራዊ ሁኔታና ተግዳሮቶች ዝርዝር ማብራሪያ የተሰጠበት ሲሆን ማብራርያዉን መሰረት ያደረገ ሀሳብ አስተያየቶች በማንሳትና የተሰጡትን ሀሳብ አስተያየቶች እንደግብዓት በመዉሰድ በቀጣይ ማሻሻያዎችን አድርጎ ወደ ስራ የማስገባት ተግባር እንደሚከናወን ተገልጿል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments