
የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን “ማርች 8” በድምቀት ተከበረ
የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን “ማርች 8” በድምቀት ተከበረ
***************
ITDB፦ መጋቢት 3/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ “ፈጣንና ቀጣይነት ያለዉ ሁሉን አቀፍ ለዉጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል”በሚል መረ ቃል በአለም ለ114ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ49ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን አቀፉ የሴቶች ቀን በድምቀት አክብሯል፡፡
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን የቢሮዉ ሀላፊዎችና ሴት ሰራተኞች በተገኙበት በተለያዩ ዝግጅቶች የተከበረ ሲሆን የቢሮ ሀላፊ አቶ ሰለሞን አማረ በዓሉ ሴቶች አሁን የደረሱበት ደረጃ ላይ ከመድረሳቸው በፊት ያሳለፉትን ትግል የሚያስቡበት እና በቀጣይም ያላሳኩትን ተግባራት ለማሳካት በቁርጠኝነት ቃል የሚገቡበትም ጭምር መሆኑን ገልፀዋል
በተያያዘም ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ የማነ ደሳለኝ ማርች 8 የሚከበርበት ዓላማ ሴቶች ተፈጥሯዊም ሆነ ስው ሰራሽ ልዩነቶች ሳያግዳቸው በርካታ ተግባራትን መፈፀም የሚያስችል አቅም እንዳላቸዉ በመጠቆም ለጋራ መብቶቻቸዉ ድምፆቸውን የሚያሰሙበት ለሴቶች ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታዎች መሻሻል አስተዋጽኦ በማድረጋቸዉ እውቅናና አክብሮት ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ከሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ተጋበዥ እንግዳ የሆኑት አቶ አቤ ወርቁ የዓለም የሴቶችን ቀን ፅንሰ ሀሳብ ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ በመስጠት በሴቶች ተወካይ የተዘጋጀዉን ኬክ በመቁረስ መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments