
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከንብረት አስተዳደር ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በየካ ክ/ከተማ እየተደረ ያለዉን የሙያ ድጋፍ ጉብኝት አድርገዋል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከንብረት አስተዳደር ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በየካ ክ/ከተማ እየተደረ ያለዉን የሙያ ድጋፍ ጉብኝት አድርገዋል
****************
ITDB፦ መጋቢት 3/2017
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እና ከንብረት አስተዳደር ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በተለያዩ የመንግስት ተቋማት ለሚከናወኑ ንብረት ጥገና እና መልሶ መጠቀም ስራ ከአስራ አንዱም ክ/ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት ለተወጣጡ አይቲ ባለሙያዎች በየተቋማቱ ያሉ ብልሽት የገጠማቸዉን የIT ማቴሪያሎችና የተለዩ የኤሌትሮኒክስ እቃዎች ጠግኖ መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ሙያዊ እገዛ በማድረግ የሀብት ብክነትን ለመከላከልና የተለያዩ ዉጤቶችን መሰረት በማድረግ በተቋማት ስር የሚገኙ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ስርዓት ላይ ችግር ፈቺ ስራዎችን መስራትና የአገልግሎት አሰጣጡን ጥራት የበለጠ ሊያጠናክር የሚችሉበትን ቀጣይነት ባለዉ ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ ላይ ይገኛል። በመሆኑም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ምህረቱ ደሳለኝና በኦፕሬሽንና አገልግሎት ዘርፍ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኦፕሬሽንና ጥገና ዳይሬክቶሬት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጥገና እና እድሳት ቡድን አባላት ጋር በጋራ በመሆን የሙያ ድጋፍ እየተደረገበት ያለዉ የካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር እና የካ ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ላይ የተሰሩ ስራዎችን ከክ/ከተማዉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ቴድሮስ ማስረሻ ጋር ተዘዋዉረዉ ምልከታ አድርገዋል።
በምልከታ ወቅት ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ምህረቱ ደሳለኝ ብልሽት የገጠማቸዉን የIT ማቴሪያሎችና የተለዩ የኤሌትሮኒክስ እቃዎች በተገቢዉ መንገድ ጥገና በማድረግ መልሰዉ አገልግሎት ላይ በመዋላቸዉ የተሰማቸዉን ደስታ ገልፀዉ የተጀመረው ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ በማሳሰብ መንግስት በጥገና ያወጣው የነበረውን ወጪ ከማስቀረት አኳያ እየተሰራ ያለው ተግባር የሚበረታታ መሆኑን አብራርተዋል። በቀጣይ ይህንን መሰል ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመላክተዋል።
የየካ ክፍለ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ቴዎድሮስ ማስረሻ የጥገና ስራው ከክፈለ ከተማው ንብረት አስተዳደር ፅ/ቤት ጋር በመተባበር ተበላሽተው አገልግሎት የማይሰጡ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን እና ላብቶፖችን መልሶ በመጠገን በርካታ የመንግስት ወጪን ማዳመቻሉን ገልፀዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments