
Addis Ababa ITDB - Innovation and Technology Development Bureau
ለግንባታና ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን የግንባታ ፈቃድ ሰርተፍኬሽን ሲስተም ለማ
******
ITDB፦የካቲት 3/2017ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የሀገራችን ቀጣይነት ያለው ዕድገት ለማስፈፀም የላቀ ሚና ካላቸው ተቋማት መካከል አንዱና ዋናው ነዉ። በመሆኑም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታና ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን የግንባታ ፈቃድ ሰርተፍኬሽን ሲስተም ማለትም የመረጃ አያያዝን የሚያዘምን ወረቀት አልባ የሆነ ከብልሹ አሰራር የፀዳ የአሰራር ስርዓት የሚዘረጋ ወጥ የሆነ ሁሉን አቀፉ ቴክኖሎጂ ያለማ ሲሆን ሲስተሙ በአስራአንዱም ክ/ከተማዎችና በስራቸዉ ያሉ ወረዳዎች ያማከለና በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የተሳካ ቅድመ ሙከራ በማካሄድ በዛሬዉ ዕለት ወደትግበራ ገብቷል።
ሲስተሙ የግንባታ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የሞባል መተግበርያ ያለዉና ተቋሙን የአገልግሎት አሰጣጥ ከፍ የሚያደርግ መሆኑ ተገልፆዋል። በመጨረሻም ባለስልጣን መስርያ ቤቱ CPSC በልፅጎ ወደ ትግበራ እንዲገባ ቢሮዉ ላደረገዉ አስተዋፅኦ የምስጋና ሠርተፍኬት ተበርክቶለታል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments