የአካባቢያቸውን ሰላም እንዲሁም ሐይማኖታዊ እና ባህላዊ በዓላትን ያለምንም የፀጥታ ችግር ለማክበር ቀንና ሌሊት አስተዋፅኦ እያበረከቱ ላሉ የሠላም ሠራዊት አካላት እውቅና የመስጠት መርሃ-ግብር ተካሄደ፡፡
ITDB፦ መስከረም/2017
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅ እና የመስቀል ደመራ፣ኢሬቻ በዓል ሐይማኖታዊ ባህላዊ ትውፊቱን ጠብቆ ያለምንም የፀጥታ ችግር ለማክበር ቀንና ሌሊት አስተዋፅኦ እያበረከቱ ላሉ የሠላም ሠራዊት አካላት እውቅና ሰጠ፡፡
በእውቅና መርሐ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ምህረት ደሳለኝ ይህ ሰላም በአጋጣሚ የመጣ ሳይሆን በነበረው ትጋትና ፅናት በተመሳሳይ የዓላማ ቁርጠኝነት ግብን ዕዉን ማድረግ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ገልፀዉ መሰናክሎች እንዴት በፅናት መፈታት እንደሚቻል ማሳያ መሆኑንና ይህም የሰላም ሠራዊት ሠላም የሁሉ ነገር መሠረት መሆኑን ተገንዝቦ አካባቢውን ብሎም ከተማውን በትጋት ጠብቆ ከሰላም ሀይሎች ጋር በጋራ በመሆን ተቀናጅተው ላሳዩት ቆራጥና ይበል የሚያሰኝ ተግባር ከልብ አመስግነዋል።
በተያያዘም የክ/ከተማ ህንፃ አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አበራ ሀገር በተለያዩ ችግሮች በምትጠቃ ጊዜ የሠላም ሰራዊት ከመንግስት እና ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በቅንጅት በመሆን ቀን ከለሊት በመስራት አንፃራዊ ሠላም እንዲገኝ ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረጉንና ቀጣይም ለሚከበሩ የመስቀል ደመራና ኢሬቻ የአደባባይ በዓላት በሰላም እንዲያልፉ በትጋት አካባቢያችንን ከወትሮ በተለየ መንገድ በመጠበቅ የሚጠበቀውን ሠላም ማስቀጠል ይኖርብናል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የወረዳው ምክትል ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ሀላፊ ብርቱ ሰዉ በበኩላቸው አንዳንድ የጥፍት ሀይሎች ብሔርን እና ሐይማኖትን ሽፋን በማድረግ የራሳቸውን የፖለቲካ ፍላጎት ለማሳካት እኩይ ተግባር ለመፈፀም ብዙ ጥረት ቢያደርጉም ይህንን ተልዕኳቸውን ለማክሸፍ የፀጥታ ሀይሉ እና የሠላም ሠራዊቱ በመቀናጀት በጋራ ስለሰሩት በጎ ተግባር የቀጠና 5 አመራር አመስግነዉ ይህ ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል በማለት ሀሳባቸዉን ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም የአካባቢያቸውን ሰላም በማስጠበቅ እና ህዝባዊና ሐይማኖታዊ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የፀጥታ ኃይሎች፣የሠላም ሠራዊት አባላት የእራት ግብዣ ተደርጓል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments