የአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የITSM ሲስተም ተግባራዊ እንዲሆን ለማስቻል ስልጠና ተሰጠ፡፡
የITSM ሲስተም ተግባራዊ እንዲሆን ለማስቻል ስልጠና ተሰጠ
******************
ITDB ነሐሴ 21/ 2016ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አሰራሩን ለማዘመን ፈጣንና ቀልጣፋ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት ያስችል ዘንድ ለዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች information technology service management (ITSM) የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ።
ITMS የተለያዩ ኦፕሬሽናል ስራዎች የሚከወኑበት በአለም አቀፍ ደረጃ እየተተገበረ የሚገኝ ስርዓት መሆኑንና በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከወረዳ እስከ ማዕከል የሚተገበር እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት ላይ ያሉ መሳሪያዎችን የሚቆጣጠር እና የሚነሱትን ጥያቄዎች ያለምንም እንግልት ከማዕከል በመሆን መፍትሄ መስጠት የሚያስችል ስርዓት መሆኑንና ከዚህም ባሻገር ምን በማን ተሰራ የሚለውን መዝግቦ የሚያስቀምጥ መሆኑን የቢሮዉ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ አስተዳደርና እድሳት ዳይሬክተር አቶ ድርሻዬ ካሰኝ ገልፀዋል።
አክለዉም ሲስተሙ የተለያዮ ሞጁሎች እንዳሉትና እነርሱም፡-
- problem management system
- change management system
- asset management system
- project management system
- contract management system
- service desk
መሆናቸዉን ገልፀዋል። በመሆኑም ሲስተሙ ወደ ተግባር ሲገባ የIT ዘርፉ ላይ ትልቅ ለዉጥ እንደሚያመጣ አመላክተዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments