የአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት...

image description
- In Technology Trends    0

የአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት ስልጠና ሰጠ

ከበይነ መረብ ጋር የተቆራኙ ቁሶች (Internet of Things - IOT) እና የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት

ከበይነ-መረብ ጋር የተቆራኙ ቁሶች (internet of things - IOT) የምንላቸው በዋናነት ሴንሰሮች እና ሶፍትዌሮች የተካተቱባቸው የቁሶች ትስስር ማለት ሲሆን በበይነ መረብ አማካኝነት ከሌሎች መሳሪያዎች እና ስርዓቶች ጋር ለመገናኘት እና መረጃን ለመለዋወጥ የሚያስችሉና በዋናነት የገመድ አልባ አዉታረ-መረብን (Wi Fi) የሚጠቀሙ ቴክኖሎጂዎች ናቸው።

ከበይነ መረብ ጋር የተቆራኙ ቁሶች (internet of things) ስራን ለማቀላጠፍና ህይወትን ቀላል ለማድረግ ትልቅ ሚና ቢኖራቸውም በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ከሚሰጡት ጥቅም በተቃራኒ ለሳይበር ደህንነት ስጋትም ተጋላጭ ሆነዉ እናገኛቸዋለን። በቁሶቹ ላይ የሳይበር ጥቃት እንዲደርስ በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም በአብዛኛው ግን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ምክንያቶች ሲከሰቱ ይስተዋላል።

• የደህንነት ክፍተት እና የግላዊነት ጉድለት ፤
• ቁሶቹ የተካተቱባቸው የዌብ ሰርቨሮች ክፍተት መኖር ፤
• የባለሁለት እና ከዚያ በላይ የባለቤትነት ማረጋገጫ ጋር በተገናኙ የሚከሰቱ ክፍተቶች፤
• አላስፈላጊ በሆኑ ፖርቶች እና ግልጽ በሆኑ ወይም ባልተመሰጠረ (ወይም ጠንካራ ባልሆነ ምስጠራ) የግንኙነት ፕሮቶኮሎች ምክንያት፤
• ደህንነታቸው ባልተጠበቀ የመረጃ ቋት፤
• ኦፕሬትንግ ሲስተም (operating system) ለማዘመን ከባድ መሆኑ፤
• ክፍተቶችን ለመዝጋት የአምራቾች ወይም የአቅራቢዎች ድጋፍ አለመኖር፤
• የመሳሪያውን የደህንነት እና የአጠቃቀም አተገባበር (manual) ጉድለት፤
• ደህንነታቸው ያልተጠበቀ የሶስተኛ ወገን ክፍሎች መካተት፤
• አካላዊ ስርቆት እና ማጭበርበር ይገኙበታል፤

በመሆኑም ተጠቃሚዎች እየተገለገሉባቸዉ ያሉትን ከበይነ መረብ ጋር የተቆራኙ ቁሶች ላይ ያለዉን አጠቃቀም ስርአት በማዘመን እና ለሳይበር ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት ሊደርሱ የሚችሉ ጥቃቶችን መከላከል ይገባል።
ምንጭ፦ INSA

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714 

See less


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments