Addis Ababa ITDB - Innovation and Technology Development Bureau
የደረጃዎች የጥራት መሰረተ ልማት (Standard and Quality Infrastructure) በተመለከተ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነዉ።
***********
ITDB ነሐሴ 23/ 2016ዓ.ም
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ፣ ከክ/ከተማ ጽ/ቤትና ከተለያዮ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለተወጣጡ 25 የIT ባለሙያዎች የደረጃዎች የጥራት መሰረተ ልማት ላይ ትኩረት ያደረገ የ10 ቀን ስልጠና በመሰጠት ላይ ነዉ።
ስልጠናዉ በኢትዮጵያ ሀገረዊ የጥራት መሰረተ ልማት ዝርጋታ እየተካሄደ በመሆኑ እንዲሁም ይህ ትግበራ ሁሉንም ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚዳስስ ከመሆኑ አንፃር በደረጃዎች የጥራት መሰረተ ልማት ላይ ግንዛቤ መፍጠር እና ተግባራዊ ማድረግ ላይ ያለመ ነዉ።
የደረጃዎች የጥራት መሰረት ከጥራት መሰረተ ልማት ጋር በተያያዘ ፈቃድ የሚሰጥ ተቋም ሲሆን፣ የኢትዮጽያ ደረጃዎች ኤጀንሲ፣ ብሔራዊ የስነ-ልኬት ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅትና የኢትዮጵያ ንግድ ስራ ፈቃድ ሰጪ አጋር ተቋማቶቹ ናቸዉ። በመሆኑም ስልጠናዉ በደረጃዎች የጥራት መሰረተ ልማት ግንዛቤን ከመፍጠር ባሻገር ከተቋማት ጋር ያለዉን ዉህደት፣ እንዴት በቅንጅት እንደሚሰራ፣ ባለድርሻ አካላቶቹስ እነማን እንደሆኑ፣ ተቋማዊ ማዕቀፉ ምን እንደሚመስል፣ ትግበራዉ ምን ተግዳሮቶች እንዳሉት፣ የተተገበረባቸዉ ሀገራት በጎ ተሞክሮ፣ እንዲሁም ከሀገራችን አዉድ አንፃር እንዴት እንደሚተገበር የሚያነሱ ሀሳቦችን ያቀፈ ስልጠና መሆኑን አሰልጣኝ አቶ አየለ ለገሰ ገልፀዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments