
Addis Ababa ITDB - Innovation and Technology Development Bureau
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሰራተኞች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በመውሰድ ላይ ይገኛሉ
*****************************
ITDB ነሀሴ 15/ 2016ዓ.ም
በኢትዮጵያና በዮናይትድ አረብ ኤምሬት መካከል በተደረገዉ ስምምነት መሰረት እንደ ሀገር የተጀመረዉን የወጣቶች የዲጅታል ክህሎት ለማሳደግና የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመስጠት፣ ሥራና ሀብት መፍጠር የሚያስችላቸዉ "የ5ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ" ኢኒሼቲቭ ተግባራዊ ለማድረግ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች መጀመሩ ይታወሳል። በመሆኑም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ5 ሚሊየነ ኮደርስ ዉስጥ 300 ሺህ ኢትዮ ኮደርስ ተጠቃሚ ለማድረግና በ2017በጀት አመት 75 ሺህ የሚሆኑ ኢትዮ ኮደሮች ለማፍራት ታቅዷል።
ይህንንም ኢኒሼቲቭ እዉን ለማድረግ ያስችል ዘንድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሰራተኞች ስልጠናዉን በመዉሰድ ላይ ይገኛሉ። ከዚህም በተጨማሪ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ እና በአካባቢዉ ለሚገኙ ነዋሪዎች የኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ የንቅናቄ መድረክ በጋራ በማዘጋጀት የዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ እና ነዋሪዉ ይህንን እድል እንዲጠቀም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ለማመቻቸት የአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በጋራ እየሰራ ይገኛል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ወጣቶች ዘመኑ የሚፈልገዉ ብቁ ዜጋ ለመሆን የሚያስችላቸዉን ይህን ስልጠና በመዉሰድ እራሳቸዉን ተወዳዳሪ ያድርጉ ሲል ቢሮዉ ጥሪውን ያስተላልፍል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments