
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ 6ተኛ ዙር አረንጓዴ አሻራ የማኖር መርሃ-ግብር ተካሄደ።
ITDB ሀምሌ 19ቀን 2016 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከክ/ከተሞች ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤቶች ጋር በጋራ በመሆን "የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትዉልድ" በሚል መሪ ቃል በንፍስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 6ተኛ ዙር አረንጓዴ አሻራ የማኖር መርሃ-ግብር ተካሂዷል።
መርሀ-ግብሩ የከተማችንን የደን ሽፍን ከፍ በማድረግ ለአየር ንብረት ለዉጥ የማትበገር ኢትዮጵያን መፍጠር ላይ ያለመ ነዉ።
በመርሀ-ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደረ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊ፣ ምክትል ቢሮ ሀላፊዎች እና የጽ/ቤት ሀላፊ እንዲሁም በክ/ከተማ የጽ/ቤት ሀላፊዎችና ባለሙያዎች በጋራ በመሆን በንፍስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሀያ ሺህ ችግኞችን ተክለዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et
ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments