የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖ...

image description
- In Technology Trends    1884

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ዉይይት ተካሄደ።

ITDB ሀምሌ 25 ቀን 2016ዓ.ም

በመርሃ-ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የንግድ ኢንዱስትሪና ባህል ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ የቢሮ ሀላፊዎችና አመራሮች እንዲሁም የክ/ከተማ ጽ/ቤት አመራሮች የተገኙ ሲሆን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊ ክቡር አቶ ሰለሞን አማረ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዉ በ2016 በጀት ዓመት በርካታ ተግባራት መከናወናቸዉን ገልፀዋል። ከዚህም ባሻገር ሶስት ዋና ዋና መመሪያዎች ፀድቀዉ ወደ ስራ የተገባበት ዓመት መሆኑን አመላክተዉ በሚቀርበዉ ዕቅድ ሆነ ሪፖርት ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የተሻለ ዉይይት እናድርግ በማለት መድረኩን በይፋ አስጀምረዋል።

በተያያዘም የ2016 ዕቅድ አፈፃፀምና የ2017 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተዉ እና የእ/በ/ዝ/ክ/ግ ቡድን መሪ አቶ መኮንን ሞጣሎ የቀረበ ሲሆን በሪፖርቱም በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ቁልፍ አበይት ተግባራት አፈፃፀም፣ የዝግጅት ምዕራፍ ስራወችን፣ የተገኙ ዉጤቶች የነበሩ ጥንካሬዎች እና ክፍተቶች፣ የተወሰዱ መፍትሄዎችና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች በዝርዝር ተዳሰዋል።

በቀረበዉ ሪፖርት ላይ ዉይይት የተካሄደ ሲሆን በዉይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የንግድ ኢንዱስትሪ ባህል ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር አቶሜ አበበ በቢሮ የተከናወኑ መልካም ተግባራት ማለትም ተቀናጅቶ መስራት፣ ተቋሙ እራሱን ለማጠናከር የሄደበት መንገድና ችግሮችን በበቂ ሁኔታ ለይቶ ለማወቅ የተከናወኑ ተግባራትን አድንቀዉ የዘርፉን ዳሬክተሮች አቅም መገንባት እና በየደረጃዉ ተገቢ ባለሙያዎች እንዲኖሩ ማድረግ፣ የተሰሩ ስራዎችን በተገቢዉ መንገድ ማስተዋወቅ እንዲሁም የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማተ ጥበቃ ላይ ትኩረት ሊሰጥባቸዉ የሚገቡ ጉዳዬች መሆናቸዉን አመላክተዋል። እንዲሁም በክ/ከተማ ጽ/ቤት አመራሮች ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች በቢሮ ሀላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

በመጨረሻም የቢሮ ሀላፊ ክቡር አቶ ሰለሞን አማረ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት ማለትም ከዘርፍ፣ ዓላማ ፈፃሚ ዳሬክተሮች፣ ድጋፍ ሰጪ ዳሬክተሮች ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች፣ ከክ/ከተማ ጽ/ቤቶች አንፃር ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ መርሀ-ግብሩ ተጠናቋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et

ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments