ለአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሰ...

image description
- In Uncategorized    0

ለአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ

ለአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ።

**************************

ITDB ሰኔ 27 ቀን 2016 ዓ.ም

ለአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ዳሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ተሰጠ።

የስልጠናዉን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተዉ ይህ ስልጠና ለዕለት ተዕለት የሰራ እንቅስቃሴ ጠቃሚና የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ላይ ግንዛቤን የሚፈጥር መሆኑን ገልፀዉ ስልጠናዉን በአግባብ መከታተል እንደሚገባ በማመላከት መልካም የስልጠና ጊዜ ተመኝተዋል።

ስልጠናዉ በአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሰዉ ሀብት አስተዳደር ዳሬክቶሬት አማካኝነት የተዘጋጀ ሲሆን ስልጠናውን የሰጡት የፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ የሰዉ ሀብት ስራ አመራር ክትትል ድጋፍ እና ኦዲት ዳሬክተር አቶ መላኩ ተመስገን ናቸው። ስልጠናዉ ትኩረት ባደረገዉ በሠራተኞች መብትና ግዴታዎች፣ የመንግስት ተቋማት ስለሚጠበቅባቸው ሃላፊነቶች በስፋት የተብራራ ሲሆን በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች በአሰልጣኙ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments