በአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የ...

image description
- In project    0

በአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የበላይነት የሚመራ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ማስጀመርያ መርሀ-ግብር ተካሄደ።

ዕለተ ረብዕ ሰኔ 12/2016 ዓ.ም 

በአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የበላይነት የሚመራ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ማስጀመርያ መርሀ-ግብር ተካሄደ። 
የመርሀ-ግብሩ ዓላማ በአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የበላይነት የሚከናወኑ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ የሚከናወንላቸዉ  ዳግማዊ ሚኒሊክ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ማስጀመሪያ ገለፃ ማድረግ ላይ ያለመ ነዉ። 

በመርሀ-ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊ ክብር  አቶ ሰለሞን አማረ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዉ ቢሮዉ የስማርት ሲቲ ስራዎችን መስራት ከጀመረ አንድ ዓመት እንደሆነዉና በዚህ አንድ ዓመት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እንደተከናወኑ ገልፀዋል። አክለዉም በቀጣይ መሰል ተግባራትን በተለያዩ ተቋማት ላይ የሚሰራ መሆኑን በማመላከት 2023-2030 የተያዘዉ ስማርት ሲቲ ኘሮጀክት አካል የሆነዉ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ስራውን የሚያከናዉኑ ተቋማት ስለፕሮጀክቱ ገለፃ እንደሚያደርጉ በማመላከት መርሀ-ግብሩን በይፋ አስጀምረዋል። 

በተያያዘም ዳግማዊ ሚኒሊክ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የመሰረተ ልማት ዝርጋታን ገለፃ ያደረጉት የባዮስ ኢንጅነሪን እና ትሬዲንግ ፒ.ኤል.ሲ ስራ አስኪያጅ አቶ ተክላይ እንዲሁም የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ የመሰረተ ልማት ዝርጋታን ገለፃ ያደረጉት የአጋዘል ትሬዲንግ አይቲ ባለሙያ አቶ ዘመንፈስ ሀ/ማርያም ሲሆኑ ገለፃዉ ትኩረት ያደረባቸዉ ርዕሰ ጉዳዮች፦
- ስለተቋማቸዉ አደረጃጀት
- በተቋማቸዉ ስለሚከናወኑ ተግባራት
- በፕሮጀክቱ ስለሚከናወኑ ኔትወርክ፣ የሰርቨርና የአይቲ መሰረተ ልማት ዝርጋታ በዝርዝር ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በተጨማሪም ተቋማቱ የክህሎት ሽግግር እንደሚያየርጉ አመላክተዋል። 

በመጨረሻም በቀረብ ፕሮጀክቶች ላይ መሰረት ያየረገ  ዉይይት የተካሄደ ሲሆን በዉይይቱ ላይ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊዎች፣ ቴክኒካል ቲሞችና የመሰረተ ልማት ዝርጋታዉ የሚከናወንላቸዉ ተቋማት የስራ ሀላፊዎች የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶችን አንስተዉ የተወያዩ ሲሆን የፊርማ ሰነ-ስርዓት በማከናወን መርሀ-ግብሩ ተጠናቋል። 

                                                    ኮሙኒኬሽን ብድን


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments