የሰኞ ማለዳ የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተከናወነ

image description
- In Training    0

የሰኞ ማለዳ የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተከናወነ

ታህሳስ 27/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ።

በመርሃ ግብሩ ላይ የቢሮው አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን አቶ ኤርሚያስ ከበደ ‘ቀጣይነት ያለው መሻሻል’ በሚል ርዕስ ላይ እውቀት ሽግርር አድርገዋል። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ አቶ ኤርሚያስ ከበደ የ’ቀጣይነት ያለው መሻሻል’ በሚል ርዕስ ስር ስለካይዘን ምንነት፣ ካይዘን ምን ምን ቦታ እንደሚያገለግል፣ ምቹ የስራ ቦታ የመፍጠር አምስት ህጎችን፣ የቀጣይነት መሻሻል ተግዳሮቶችን፣ በቀጣይነት መሻሻል ውስጥ ሊታዩ የሚችሉትን ሰባት እክሎችን እና እክሎችን የማስወገድ ፋይዳ በስፋት አስረድተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አዋሌ መሐመድ ገለፃውን ያቀረቡት አቶ ኤርሚያስን በማመስገን በቀጣይነት ትኩረት የሚፈልጉትንና መጠናቀቅ የሚገባቸውን ስራዎች በማመላከት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

#AddisSmartcity

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments