የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ

image description
- In Training    0

የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ

ITDB፦ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሳምንታዊው የወርቃማ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡ በዚህ መርሃ ግብር ላይ የቢሮው አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን የእዉቀት ሽግግሩን ያደረጉት የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ 5ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ የ2018 ዕቅድ፣ የ2018 በጀት ዓመት ተቋማት የሚያከናወኑት ዕቅድ፣ አጠቃላይ አፈፃፀም በስልጠና አይነትና የክልሎች አጠቃላይ አፈፃፀም ላይ ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም ኢትዮ ኮደርስን በተመለከተ መዲናችን ከክልሎች የተሻለ አፈፃፀም እንዳላትና ከዚህም ባሻገር የተሻለች ከተማና ሀገርን ለመገንባት ሁላችንም በተሰማራንበት የስራ መስክ ዉጤታማ መሆን እንደሚጠበቅብን ገልፀዉ በሳምንቱ የሚከናወኑ ተግባራት ዝርዝር በመማመላከት መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments