የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት 2ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በአዲስ አበባ የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተገመገመ
ITDB፦ ታህሳስ 20/ 2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከሚደግፋቸዉ ዘጠኝ ተቋማት መካከል አንዱ ነው። በመሆኑም የግምገማ ዓላማ የቢሮው የ2018 ሁለተኛ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ተግባራት መገምገምና ክፍተቶች ካሉ ድጋፍ ማድረግ ላይ ያለመ ነው።
የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ 5ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ የ2018 ዕቅድ፣ የ2018 በጀት ዓመት ተቋማት የሚያከናወኑት ዕቅድ፣ አጠቃላይ አፈፃፀም በስልጠና አይነትና የክልሎች አጠቃላይ አፈፃፀም በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን የቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተው የ2018 በጀት ዓመት የመጀመርያ 6ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን የቀረበዉ ሪፖርት ላይ መሰረት በማድረግ ከቋሚ ኮሚቴው አባላት የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች ተነስተዋል። ከነህም መካከል
የለሙ ሲስለሞች ላይ የሚስተዋሉ የኔትወርክ መቆራረጥን ለማስቀረት ምን እየተደረገ ነዉ፣ ኮምንኬሽን በተመለከተ ከሬድዮ ቴሌቪዥን እና ጋዜጣ ባሻገር ዲጅታል ሚዲያዉን በተገቢዉ መንገድ ከመጠቀም አንፃር ምን እየተካሄደ ነዉ፣ ክላዉድ ዳታሴንተርን ምን ያህል ትኩረት እየተደረገ ነዉ፣ አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ምን ደረጃ ላይ ነዉ፣ ከሳይበር ደህንነት ጋር በተያያዘ ምን አይነት የጥንቃቄ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነዉ፣ የሰዉ ሀይልን በተገቢዉ ለመሟላት ያጋጠሙ ችግሮች ምንድናቸዉ፣ ወሳኝ ኩነት ላይ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ለማስቀረት ምን እየተካሄደ ነዉ፣ ብራንዲንግ ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚገባ የሚሉ ርዕሰ ጉዳዬች በዋናነት ተነስተዋል።
በተነሱ ሀሳብ አስተያየቶች ላይ የሚመለከታቸዉ አካላትና ም/ቢሮ ሀላፊዎችና ፅ/ቤት ሀላፊ ምላሽ የሰጡበት ሲሆን የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ጋትዌች በነበራቸዉ ቆይታ ደስተኛ እንደነበሩና ቢሮዉለለ ለምናየዉ የቴክኖሎጂ ለዉጥ ሁሉ መሰረት መሆኑን ገልፀዉ ክፍተት የማስተዋልባቸዉ አንዳንድ ጉዳዮች ላዬ በቀጣይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚገባ አመላክተለለዋል። በመጨረሻም ቢሮዉ ያደራጀዉን ስማርት ጋለለሪና የለሙ ሲስተሞችን ተዘዋዉረዉ ተመልክተዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments