በአገልግሎት አሰጣጥና በተግባቦት ክህሎት ላይ መ...

image description
- In Training    0

በአገልግሎት አሰጣጥና በተግባቦት ክህሎት ላይ መሰረት ያደረገ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነዉ

ITDB፦ ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በአገልግሎት አሰጣጥና በተግባቦት ክህሎት ላይ መሰረት ያደረገ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነዉ።

የስልጠናውን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን ስልጠናው ክህሎታችንንና ስራ ላይ ያለንን አቅም መሬት አዉርደን የምንጠቀምበት የምናሳድግበት እራሳችንን አንድ ደረጃ ከፍ የምናደርግበት መሆኑን ገልፀው ስልጠናውን በአግባቡ መከታተል እንደሚገባ በማመላከት ስልጠናዉን ላዘጋጁ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ስልጠናዉ በሰዉ ሀብት ዳይሬክቶሬት አማካኝነት በሁለት ዙር የተዘጋጀ ሲሆን የስልጠናዉ ዋና ዓላማ ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥን እና የተግባቦት ክህሎት ፅንሰ ሀሳብ ላይ የተሻለ መረዳት በመፍጠር የአገልግሎት አሰጣጥና የተግባቦት ክህሎት ተግዳሮቶች የመለየትና ማሻሻል ስልቶች የመደገፍ ክህሎት ማዳበር ማሳደግ እንዲሁም በተገልጋይ አያያዝና ቅሬታ አፈታት ዙርያ የተሻለ ክህሎት እንዲኖር ማድረግ ነዉ።

ስልጠናዉን የሰጡት አሰልጣኝ አቶ አለማየሁ ግርማ የአገልግሎት አሰጣጥ ፅንሰ ሀሳብ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ መርሆዎች፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ስልቶችና ዉጤታማ የተግባቦት ክህሎት ላይ በምሳሌ በማስደገፍ አሳታፊ የሆነ በዝርዝር ማብራሪያ የተደገፈ ስልጠና የሰጡ ሲሆን ስልጠናዉ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments